Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ቆሮንቶስ 8:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 አንተ አማኙ በጣ​ዖት ቤት በማ​ዕድ ተቀ​ም​ጠህ ያየህ ቢኖር ያ ልቡ ደካማ የሆነ ሰው ወዲ​ያው ለጣ​ዖት የተ​ሠ​ዋ​ውን ደፍሮ ይበ​ላል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 አንተ ይህን የመሰለ ዕውቀት ኖሮህ፣ ደካማ ኅሊና ያለው ሰው በቤተ ጣዖት ስትበላ ቢያይህ፣ ለጣዖት የተሠዋውን ምግብ ለመብላት አይደፋፈርምን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 አንተ ዕውቀት ያለህ በጣዖት ቤት በማዕድ ስትቀመጥ አንድ ሰው ቢያይህ፥ ደካማ ሰው ቢሆን ለጣዖት የተሠዋውን ለመብላት ሕሊናው አይደፋፈርምን?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 “ዕውቀት አለኝ” ብለህ ለጣዖት የተሠዋውን በቤተ ጣዖት ስትበላ በእምነቱ ያልጠነከረ ሰው ቢያይህ ይህ ድርጊትህ ሰውየው ለጣዖት የተሠዋውን እንዲበላ ያደፋፍረው የለምን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 አንተ እውቀት ያለህ በጣዖት ቤት በማዕድ ስትቀመጥ አንድ ሰው ቢያይህ፥ ደካማ ሰው ቢሆን ለጣዖት የተሠዋውን ለመብላት ሕሊናው አይታነጽበትምን?

Ver Capítulo Copiar




1 ቆሮንቶስ 8:10
13 Referencias Cruzadas  

ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም አስ​ረው ለመ​ሥ​ዊ​ያው መጋ​ረጃ ያደ​ር​ጋሉ፤ በአ​ም​ላ​ካ​ቸ​ውም ቤት የቅ​ሚያ ወይን ጠጅ ይጠ​ጣሉ።


ሕዝ​ቡ​ንም ወደ አም​ላ​ኮ​ቻ​ቸው መሥ​ዋ​ዕት ጠሩ፤ ሕዝ​ቡም መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውን በሉ፤ ለአ​ም​ላ​ኮ​ቻ​ቸ​ውም ሰገዱ።


ነገር ግን ለጣ​ዖት ከሚ​ሠ​ዋው፥ ከዝ​ሙት፥ ሞቶ የተ​ገ​ኘ​ው​ንና ደም ከመ​ብ​ላት እን​ዲ​ርቁ፥ ለራ​ሳ​ቸው የሚ​ጠ​ሉ​ት​ንም በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ላይ እን​ዳ​ያ​ደ​ርጉ እዘ​ዙ​አ​ቸው።


በራሱ ርኩስ የሆነ ነገር እን​ደ​ሌለ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ሆኜ ዐው​ቄ​አ​ለሁ፤ ተረ​ድ​ቼ​አ​ለ​ሁም፤ ነገር ግን ማና​ቸ​ውም ነገር ርኩስ እን​ደ​ሚ​ሆን ለሚ​ያ​ስብ ያ ለእ​ርሱ ርኩስ ነው።


የሚ​ጠ​ራ​ጠር ግን ቢበላ ይፈ​ረ​ድ​በ​ታል፤ በማ​መን አል​ሆ​ነ​ምና፤ ያለ እም​ነ​ትም የሚ​ደ​ረግ ሁሉ ኀጢ​አ​ትና በደል ነው።


ለአ​ይ​ሁ​ድም፥ ለአ​ረ​ማ​ው​ያ​ንም፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንም ያለ ማሰ​ና​ከል አር​አያ ሁኑ​አ​ቸው።


ለጣ​ዖ​ታት የተ​ሠ​ዋ​ውን ስለ​መ​ብ​ላት ግን ጣዖት ሁሉ በዓ​ለም ከንቱ እን​ደ​ሆነ፥ ከአ​ንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በቀር ሌላ አም​ላክ እን​ደ​ሌለ እና​ው​ቃ​ለን።


ነገር ግን ሁሉ የሚ​ያ​ው​ቀው አይ​ደ​ለም፤ እስከ ዛሬ በጣ​ዖ​ታት ልማድ፥ ለጣ​ዖት የተ​ሠ​ዋ​ውን የሚ​በሉ አሉ፤ ኅሊ​ና​ቸ​ውም ደካማ ስለ​ሆነ ይረ​ክ​ሳል።


ነገር ግን እና​ን​ተን በማ​የት ሌላው እን​ዳ​ይ​ሰ​ና​ከል ተጠ​ን​ቀቁ።


ወደ እር​ሻ​ውም ወጡ፤ ወይ​ና​ቸ​ው​ንም ለቀሙ፤ ጠመ​ቁ​ትም፤ የደ​ስ​ታም በዓል አደ​ረጉ፤ ወደ አም​ላ​ካ​ቸ​ውም ቤት ገቡ፤ በሉም፤ ጠጡም፤ አቤ​ሜ​ሌ​ክ​ንም ረገ​ሙት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos