የቤቱንም አዛዥ ኤልያቄምን ጸሓፊውንም ሳምናስን የካህናቱንም አለቆች ማቅ ለብሰው ወደ አሞጽ ልጅ ወደ ነቢዩ ኢሳይያስ ይሄዱ ዘንድ ላካቸው።
ኤርምያስ 19:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፥ “ሂድ፤ የሸክላ ሠሪ የሠራውን ገምቦ ግዛ፤ ከሕዝቡም ሽማግሌዎችና ከካህናት ሽማግሌዎች ከአንተ ጋር ውሰድ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ሄደህ፣ ከሸክላ ሠሪ ገንቦ ግዛ፤ ከሕዝቡና ከካህናቱ መካከል ሽማግሌዎች የሆኑትን አንዳንዶቹን ይዘህ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም እንዲህ አለኝ፦ “ሂድ፥ ከሸክላ ሠሪ ገምቦ ግዛ፥ ከሕዝቡም ሽማግሌዎችና ከካህናት ሽማግሌዎች ከአንተ ጋር ውሰድ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “ሄደህ ከሸክላ ሠሪው ገንቦ ግዛ፤ ከሕዝቡና ከካህናቱ መካከል ታላላቆቹን መርጠህ ከአንተ ጋር አብረው እንዲሄዱ አድርግ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፦ ሂድ፥ ከሸክላ ሠሪ ገምቦ ግዛ፥ ከሕዝቡም ሽማግሌዎችና ከካህናት ሽማግሌዎች ከአንተ ጋር ውሰድ፥ |
የቤቱንም አዛዥ ኤልያቄምን ጸሓፊውንም ሳምናስን የካህናቱንም አለቆች ማቅ ለብሰው ወደ አሞጽ ልጅ ወደ ነቢዩ ኢሳይያስ ይሄዱ ዘንድ ላካቸው።
አወዳደቁም እንደ ሸክላ ሠሪ ገንቦ የደቀቀ ይሆናል፤ ሳይራራም ያደቅቀዋል፤ ከስባሪውም እሳት ከማንደጃ የሚወስዱበት፥ ወይም ውኃ ከጕድጓድ የሚቀዱበት ገል አይገኝም።”
እግዚአብሔር እንዲህ ይለኛል፦ ሂድ፥ ከተልባ እግር የተሠራችን መታጠቂያ ለአንተ ግዛ፤ ወገብህንም ታጠቅባት፤ በውኃውም ውስጥ አትንከራት።
“የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ብዙ ቀን ይጠበቅ ዘንድ የታተመውን ይህን የውል ወረቀት ወስደህ በሸክላ ዕቃ ውስጥ አኑረው።
“አንተም የሰው ልጅ ሆይ! ራስን ከሚላጭ ምላጭ ይልቅ የተሳለ ጐራዴን ውሰድ፤ ወስደህም በእርስዋ ራስህንና ጢምህን ተላጭ፤ ሚዛንንም ውሰድ፤ ጠጕሩንም ትከፋፍለዋለህ።
ሽማግሌውንና ጎበዙን፥ ድንግሊቱንም፥ ሕፃናቱንና ሴቶቹን፥ ፈጽማችሁ ግደሉ፤ ነገር ግን ምልክቱ ወደ አለበት ሰው ሁሉ አትቅረቡ፤ በመቅደሴም ጀምሩ” አላቸው። በቤቱም አንጻር ባሉ ሽማግሌዎች ጀመሩ።
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “ከእስራኤል ሽማግሌዎች፥ ለሕዝቡ ሽማግሌዎችና ጸሐፍት ይሆኑ ዘንድ የምታውቃቸውን፥ ሰባ ሰዎች ሰብስብልኝ፤ ወደ ምስክሩም ድንኳን አምጣቸው፤ በዚያም ከአንተ ጋር አቁማቸው።
ወደ እኛም መጣና የጳውሎስን መታጠቂያ አንሥቶ እጁንና እግሩን በገዛ እጁ አስሮ እንዲህ አለ፥ “መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ይላል፤ የዚህን መታጠቂያ ጌታ አይሁድ በኢየሩሳሌም እንዲህ ያስሩታል፤ ለአሕዛብም አሳልፈው ይሰጡታል።”