ከዚህ በኋላ ኤልያስ ተነሥቶ፥ እነሆ፥ በራሱ አጠገብ የተጋገረ እንጎቻና በማሰሮ ውኃ አገኘ። በላም፤ ጠጣም፤ ተመልሶም ተኛ።
ኢሳይያስ 33:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱ ከፍ ባለ በጽኑዕ ዓለት ዋሻ ይኖራል፤ እንጀራም ይሰጠዋል፤ ውኃውም የታመነች ትሆናለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህ ሰው በከፍታ ላይ ይኖራል፤ የተራራም ምሽግ መጠጊያው ይሆናል፤ እንጀራ ይሰጠዋል፣ ውሃውም አይቋረጥበትም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ ከፍ ባለ ሥፍራ ይቀመጣል፤ ጠንካራ አምባ መጠጊያው ይሆናል፤ እንጀራም ይሰጠዋል፥ ውኃውም የማታቋርጥ ትሆናለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በከፍተኛ ቦታ ላይ ይኖራሉ። ከለላቸውም እንደ ቋጥኝ ምሽግ ይሆናል ምግባቸውንም በጊዜው ያገኛሉ፤ የሚጠጡትንም ውሃ አያጡም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱ ከፍ ባለ ሥፍራ ይቀመጣል፥ ጠንካራ አምባ መጠጊያው ይሆናል፥ እንጀራም ይሰጠዋል፥ ውኃውም የታመነች ትሆናለች። |
ከዚህ በኋላ ኤልያስ ተነሥቶ፥ እነሆ፥ በራሱ አጠገብ የተጋገረ እንጎቻና በማሰሮ ውኃ አገኘ። በላም፤ ጠጣም፤ ተመልሶም ተኛ።
አጥንቶች ሁሉ እንዲህ ይሉሃል፦ “አቤቱ፥ እንደ አንተ ማን ነው? ድሃውን ከሚቀማው እጅ ድሃውንና ችግረኛውንም ከሚነጥቀው እጅ ታድነዋለህ።”
ለተዋረዱ ሰዎች ከተሞች ረዳት ሆነሃልና፥ በችግራቸው የተጨነቁትን በደስታ ጋረድሃቸው፤ ከክፉዎች ሰዎችም አዳንሃቸው፤ ለተጠሙት ጥላ ሆንሃቸው፤ ለተገፉትም ሕይወት ሆንሃቸው።
እግዚአብሔርም የጭንቀትን እንጀራና የመከራን ውኃ ይሰጥሃል። የሚያሳስቱህም እንግዲህ ወደ አንተ አይቀርቡም፤ ዐይኖችህ ግን የሚያሳስቱህን ያያሉ፤
የሚራራላቸውም ያጽናናቸዋልና፥ በውኃ ምንጮችም በኩል ይመራቸዋልና አይራቡም፤ አይጠሙም፤ የፀሐይ ትኩሳትም አይጐዳቸውም።
በዚያን ጊዜ በእግዚአብሔር ትታመናለህ፤ በምድርም በረከት ላይ ያወጣሃል፤ የአባትህ የያዕቆብንም ርስት ይመግብሃል፤ የእግዚአብሔር አፍ እንደዚህ ተናግሮአልና።
ንጉሡም ሴዴቅያስ አዘዘ፤ ኤርምያስንም በግዞት ቤቱ ቅጥር ግቢ አኖሩት፤ እንጀራም ሁሉ ከከተማ እስኪጠፋ ድረስ ዕለት ዕለት አንድ አንድ እንጀራ ከውጪ ጋጋሪዎች እያመጡ ይሰጡት ነበር። እንዲሁም ኤርምያስ በግዞት ቤት ቅጥር ግቢ ተቀምጦ ነበር።
እግዚአብሔርም በጽዮን ሆኖ ድምፁን ከፍ አድርጎ ይጮኻል፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ቃሉን ይሰጣል፤ ሰማይና ምድርም ይናወጣሉ፤ እግዚአብሔር ግን ለሕዝቡ ይራራል፤ የእስራኤልንም ልጆች ያጸናል።
እስራኤል ሆይ ብፁዕ ነህ፤ በእግዚአብሔር የዳነ ሕዝብ እንደ አንተ ማንነው? እርሱ ያጸንሃል፤ ይረዳሃልም፤ ትምክሕትህ በሰይፍህ ነው፤ ጠላቶችህ ውሸታሞች ናቸው፤ አንተም በአንገታቸው ላይ ትጫናለህ።”