ኢሳይያስ 21:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ ምድረ በዳ የተነገረ ቃል፤ ዐውሎ ነፋስ በምድረ በዳ እንደሚያልፍ፥ እንዲሁ ከሚያስፈራ ሀገር ከምድረ በዳ ይመጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በባሕሩ ዳር ባለው ምድረ በዳ ላይ የተነገረ ንግር፤ ዐውሎ ነፋስ ከደቡብ እየጠራረገ እንደሚመጣ፣ ወራሪ ከአሸባሪ ምድር፣ ከምድረ በዳ ይመጣል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በባሕር አጠገብ ስላለው ስለ ምድረ በዳ የተነገረ ትንቢት። ዐውሎ ነፋስ ከደቡብ እንደሚወጣ፥ እንዲሁ ከሚያስፈራ አገር ከምድረበዳ ይወጣል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በባሕር አጠገብ ስለሚገኝ ምድረ በዳ የተነገረ የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው። ከደቡብ በኩል የሚመጣው ዐውሎ ነፋስ ሁሉን ነገር ጠራርጎ እንደሚወስድ አስፈሪ ከሆነች ከአንዲት አገር ከባድ ጥፋት ይመጣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በባሕር አጠገብ ስላለው ስለ ምድረ በዳ የተነገረ ሸክም። ዐውሎ ነፋስ ከደቡብ እንደሚወጣ፥ እንዲሁ ከሚያስፈራ አገር ከምድረ በዳ ይወጣል። |
ስለዚህ በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር መዓት በጽኑ ቍጣው ቀንም ሰማያት ይንቀጠቀጣሉ፤ ምድርም ከመሠረቷ ትናወጣለች።
እግዚአብሔርም ያዕቆብን ይምረዋል፤ እስራኤልንም ደግሞ ይመርጠዋል፤ በሀገራቸውም ያርፋሉ፤ መጻተኞችም ከእነርሱ ጋር አንድ ይሆናሉ፤ ከያዕቆብም ቤት ጋር ይጨመራሉ።
“ባቢሎንን የወፎች መኖሪያ አደርጋታለሁ፤ እንደ ኢምንትም ትሆናለች፤ በጥፋትም እንደ ረግረግ ጭቃ አደርጋታለሁ” ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
አንቺ ድንግል የባቢሎን ልጅ ሆይ፥ ውረጂ፤ በትቢያም ላይ ተቀመጪ፤ የከለዳውያን ሴት ልጅ ሆይ፥ ከዚህ በኋላ ለስላሳና ቅምጥል አትባዪምና ያለ ዙፋን በመሬት ላይ ተቀመጪ።
ፍላጾቻቸው ተስለዋል፤ ቀስቶቻቸውም ሁሉ ተለጥጠዋል፤ የፈረሶቻቸውም ኮቴ እንደ ቡላድ፥ የሰረገሎቻቸውም መንኰራኵር እንደ ዐውሎ ነፋስ ይቈጠራል።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እነሆ፥ በባቢሎን ላይና በከለዳውያን ምድር በሚኖሩት ላይ የሚያቃጥልና የሚያጠፋ ነፋስን አስነሣለሁ።
ስድባችንን ስለ ሰማን አፍረናል፤ ባዕዳን ሰዎችም ወደ ቤተ መቅደሳችን ወደ እግዚአብሔር ቤት ገብተዋልና ውርደት ፊታችንን ከድኖታል።
እኔም አየሁ፤ እነሆም ከሰሜን በኩል ዐውሎ ነፋስና ታላቅ ደመና፥ የሚበርቅም እሳት መጣ፤ በዙሪያውም ፀዳል ነበረ፤ በመካከልም በእሳቱ ውስጥ የሚብለጨለጭ ነገር ነበረ።
እርሱና ሕዝቡ የአሕዛብም ኀያላን ምድሪቱን ለማጥፋት ይላካሉ፤ ግብፃውያንንም በሰይፍ ይወጉአቸዋል፤ ምድሪቱም በሙታን ትሞላለች።
የሌላ ሀገር ሰዎች፥ የአሕዛብ ጨካኞች የሆኑ፥ ቈርጠው ጣሉት፤ በተራሮችና በሸለቆዎች ሁሉ ውስጥ ጫፎቹ ወደቁ፤ ቅርንጫፎቹም በምድር ፈሳሾች ሁሉ ላይ ተሰባበሩ፤ የምድርም አሕዛብ ሁሉ ከጥላው ተመልሰው ተዉት።
እንደ ዝናም ትወጣለህ፤ እንደ ደመናም ምድርን ትሸፍን ዘንድ ትደርሳለህ፤ አንተም ከብዙ ሕዝብና ሠራዊት ጋር ትወድቃለህ።”
እግዚአብሔርም በእነርሱ ላይ ይገለጣል፥ ፍላጻውም እንደ መብረቅ ይወጣል፣ ጌታ እግዚአብሔርም መለከትን ይነፋል፥ በደቡብም ዐውሎ ነፋስ ይሄዳል።