La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢሳይያስ 17:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ተክ​ልን በተ​ከ​ል​ህ​በት ቀን ትበ​ድ​ላ​ለህ፤ የዘ​ራ​ኸ​ውም በበ​ነ​ጋው በም​ታ​ወ​ር​ስ​በት ቀን ይበ​ቅ​ላል፤ አባ​ትም ለልጁ እን​ደ​ሚ​ያ​ወ​ርስ አን​ተም ለል​ጆ​ችህ ታወ​ር​ሳ​ለህ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በተከልህበት ቀን እንዲበቅል፣ በዘራህበትም ማግስት እንዲያብብ ብታደርግ እንኳ፣ መከሩ በደዌና በማይሽር ሕመም ቀን፣ እንዳልነበረ ይሆናል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በተከልክበት ቀን እንዲበቅል፥ በዘራህበት ማግስት እንዲያብብ ብታደርግ እንኳን፥ ነገር ግን በኀዘንና በብርቱ ደዌ ቀን መከሩ እንዳልነበር ይሆናል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በዚያው በተከላችሁት ቀን አድጎ ቢያብብ እንኳ ከቶ አታመርቱትም፤ በዚህ ፈንታ የምታመርቱት ችግርና የማይፈወስ በሽታ ይሆናል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በተከልህበት ቀን ታበቅለዋለህ፥ በነጋውም ዘርህን እንዲያብብ ታደርገዋለህ፥ ነገር ግን በኀዘንና በትካዜ ቀን መከሩ ይሸሻል።

Ver Capítulo



ኢሳይያስ 17:11
18 Referencias Cruzadas  

እኔ እን​ዳ​የሁ፥ ኀጢ​ኣ​ትን የሚ​ያ​ርሱ፥ የሚ​ዘ​ሩ​አ​ትም መከ​ራን ለራ​ሳ​ቸው ያጭ​ዳሉ።


በጨ​ለማ ከሚ​ሄድ ክፉ ሥራ፥ ከአ​ደ​ጋና ከቀ​ትር ጋኔን አት​ፈ​ራም።


አጫጅ የቆ​መ​ውን እህል ሰብ​ስቦ ዛላ​ውን እን​ደ​ሚ​ያ​ጭድ ይሆ​ናል፤ በሸ​ለቆ እሸ​ትን እን​ደ​ሚ​ሰ​በ​ስ​ብም እን​ዲሁ ይሆ​ናል።


ነቢ​ያት በሐ​ሰት ትን​ቢት ይና​ገ​ራሉ፥ ካህ​ና​ትም በእ​ጃ​ቸው ያጨ​በ​ጭ​ባሉ፥ ሕዝ​ቤም እን​ዲህ ያለ​ውን ነገር ይወ​ድ​ዳሉ፤ በፍ​ጻ​ሜ​ውስ ምን ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ?


ነፋ​ስን ዘር​ተ​ዋ​ልና ዐውሎ ነፋ​ስን አጨዱ፤ ለነ​ዶ​አ​ቸ​ውም ኀይል የለ​ውም፤ ከፍ​ሬ​ውም ዱቄት አይ​ገ​ኝም፤ ቢገ​ኝም ጠላት ይበ​ላ​ዋል።


ኤፍ​ሬም ታመመ፤ ሥሩም ደረቀ፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ ፍሬ አያ​ፈ​ራም፤ ደግ​ሞም ቢወ​ልዱ የተ​ወ​ደ​ደ​ውን የማ​ኅ​ፀ​ና​ቸ​ውን ፍሬ እገ​ድ​ላ​ለሁ።


ጊደ​ሮች ከም​ሳ​ጋ​ቸው ጠፉ፤ ጎተ​ራ​ዎች ባዶ ሆኑ፤ ዐው​ድ​ማ​ዎ​ቹም ፈራ​ረሱ፤ እህሉ ደር​ቆ​አ​ልና።


ጕል​በ​ታ​ች​ሁም በከ​ንቱ ያል​ቃል፤ ምድ​ራ​ች​ሁም እህ​ል​ዋን አት​ሰ​ጥም፤ የዱር ዛፎ​ችም ፍሬ​ያ​ቸ​ውን አይ​ሰ​ጡም።


ነገር ግን ልቡ​ና​ህን እንደ ማጽ​ና​ትህ፥ ንስ​ሓም እንደ አለ​መ​ግ​ባ​ትህ መጠን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እው​ነ​ተና ፍርድ በሚ​ገ​ለ​ጥ​በት ቀን መቅ​ሠ​ፍ​ትን ለራ​ስህ ታከ​ማ​ቻ​ለህ።


ወይን ትተ​ክ​ላ​ለህ፤ ታበ​ጀ​ው​ማ​ለህ፤ ከወ​ይ​ኑም አት​ጠ​ጣም፤ ክፉ ትልም ይበ​ላ​ዋ​ልና በእ​ርሱ ደስ አይ​ል​ህም።