እርሱም አለ፥ “እንዲህ አይደለም፤ እስራኤል ሁሉ ጠባቂ እንደሌላቸው በጎች በተራሮች ላይ ተበትነው አየሁ፤ እግዚአብሔርም አለ፦ እግዚአብሔር የእነዚህ አምላክ አይደለምን? እያንዳንዱ በሰላም ወደ ቤቱ ይመለስ።”
ኢሳይያስ 13:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የተረፉትም ሁሉ እንደ ተባረረ ሚዳቋ፥ እንደ ባዘነ በግም ይሆናሉ። የሚሰበስባቸውም የለም፤ እንዲሁም ሰው ሁሉ ወደ ወገኑ ይመለሳል፤ ሁሉም ሰው ወደ ሀገሩ ይሸሻል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደሚታደን ሚዳቋ፣ እረኛም እንደሌለው የበግ መንጋ፣ እያንዳንዱ ወደ ወገኑ ይመለሳል፣ እያንዳንዱም ወደ አገሩ ይሸሻል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደሚታደን ሚዳቋ፤ እረኛም እንደሌለው የበግ መንጋ፤ እያንዳንዱ ወደ ወገኑ ይመለሳል፤ እያንዳንዱም ወደ አገሩ ይሸሻል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አዳኝ እንዳባረረው አጋዘንና ጠባቂ እንደሌለው የበግ መንጋ ይባዝን የነበረው እያንዳንዱ ሰው ወደ ወገኖቹ ይመለሳል፤ ወደ አገሩም ይሸሻል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደ ተባረረም ሚዳቋ፥ ማንም እንደማይሰበስበው እንደ በግ መንጋ፥ ሰው ሁሉ ወደ ወገኑ ይመለሳል፥ ሁሉም ወደ አገሩ ይሸሻል። |
እርሱም አለ፥ “እንዲህ አይደለም፤ እስራኤል ሁሉ ጠባቂ እንደሌላቸው በጎች በተራሮች ላይ ተበትነው አየሁ፤ እግዚአብሔርም አለ፦ እግዚአብሔር የእነዚህ አምላክ አይደለምን? እያንዳንዱ በሰላም ወደ ቤቱ ይመለስ።”
ፀሐይም በገባች ጊዜ አዋጅ ነጋሪው ወጥቶ፥ “ንጉሡ ሞቶአልና እያንዳንዱ ወደ ከተማው፥ እያንዳንዱም ወደ ሀገሩ ይሂድ” ብሎ አዋጅ ነገረ።
ብዙዎች አሕዛብ እንደ ብዙ ውኃ ናቸው፤ ከፏፏቴ ውስጥ በኀይል እንደሚወርድ እንደ ብዙ ውኃ ፈሳሽ ይጮኻሉ፤ ያጠፉታልም፤ እነርሱም ከሩቅ ይወርዳሉ፤ በተራራም ላይ እንዳለ እብቅ፥ በነፋስ ፊት ዐውሎ ነፋስ እንደሚያዞረው እንደ መንኰራኵር ትቢያም ይበተናሉ።
እንጀራ ይዛችሁ ከሰልፍ ከሸሹ ከብዙ ሰዎችና በጦር ከጠፉ ከብዙ ሰዎች፥ ፍላጻ ከያዙ ከብዙ ሰዎችና ጦር ከያዙ ከብዙ ሰዎች፥ ቀስቶቻቸው ከተሳቡና በሰልፍ ከወደቁ ከብዙ ሰዎች ያመለጡትን ተቀበሏቸው።
“ሰባው ዓመትም በተፈጸመ ጊዜ፥ የባቢሎንን ንጉሥና ያን ሕዝብ ስለ ኀጢአታቸው እቀጣለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ የከለዳውያንንም ምድር ለዘለዓለም አጠፋቸዋለሁ።
ዘሪውንና በመከር ጊዜ ማጭድ የሚይዘውን ከባቢሎን አጥፉ፤ ከአረማዊው ሰይፍ ፊት የተነሣ እያንዳንዱ ወደ ወገኑ ይመለሳል፤ እያንዳንዱም ወደ ሀገሩ ይሸሻል።
ባቢሎንን ፈወስናት፥ እርስዋ ግን አልተፈወሰችም፤ ፍርድዋ እስከ ሰማይ ደርሶአልና፥ እስከ ከዋክብትም ድረስ ከፍ ከፍ ብሎአልና፥ እንተዋት፤ ሁላችንም ወደ ሀገራችን እንሂድ።