ሆሴዕ 10:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤፍሬምም ቀንበርን እንደ ለመደች ጊደር ነው፤ እኔ ግን በአንገቱ ውበት እጫንበታለሁ፤ በኤፍሬም ላይ እጠምድበታለሁ፤ ይሁዳንም እለጕመዋለሁ፤ ያዕቆብም ለራሱ መንግሥትን ያስተካክላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤፍሬም ማበራየት እንደምትወድድ፣ እንደ ተገራች ጊደር ነው፤ በተዋበ ጫንቃዋም ላይ፣ ቀንበርን አኖራለሁ፤ ኤፍሬምን እጠምዳለሁ፤ ይሁዳ ያርሳል፤ ያዕቆብም መሬቱን ያለሰልሳል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤፍሬም ማበራየት የምትወድ የተገራች ጊደር ነበር፥ እኔም በውብ አንገትዋ ላይ አልጫንኩባትም፤ በኤፍሬም ላይ እጠምድበታለሁ፥ ይሁዳም ያርሳል፥ ያዕቆብም ለራሱ አፈሩን ያለሰልሳል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እስራኤል ማበራየት እንደምትወድ ጊደር ነበረች፤ ነገር ግን በተዋበ ጫንቃዋ ላይ ቀንበር እጭንበታለሁ፤ በዚህ ዐይነት ይሁዳ ያርሳል፤ የያዕቆብ ልጆች በሙሉ ተጠምደው መሬቱን ያለሰልሳሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤፍሬም ማበራየት እንደ ለመደች ጊደር ነው፥ እኔ ግን በአንገቱ ውበት እጫንበታለሁ፥ በኤፍሬም ላይ እጠምድበታለሁ፥ ይሁዳም ያርሳል፥ ያዕቆብም አፈሩን ያለሰልሳል። |
የእስራኤልም አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር ይገዙለት ዘንድ የብረትን ቀንበር በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ አንገት ላይ አድርጌአለሁ፤ እነርሱም ይገዙለታል፤ የምድረ በዳ አራዊትን ደግሞ ሰጥቼዋለሁ።”
“ርስቴን የምትበዘብዙ እናንተ ሆይ! ደስ ብሎአችኋልና፥ ሐሤትንም አድርጋችኋልና፥ በመስክ ላይም እንዳለች ጊደር ሆናችሁ ተቀናጥታችኋልና፥ እንደ ብርቱዎችም በሬዎች ቷጋላችሁና፤
በሰው ገመድ በፍቅርም እስራት ሳብኋቸው፤ ለእነርሱም ፊቱን በጥፊ እንደሚመቱት ሰው ሆንሁላቸው፤ ወደ እርሱም እመለከታለሁ፤ እችለውማለሁ።
እናታቸው አመንዝራለችና፤ የወለደቻቸውም፥ “እንጀራዬንና ውኃዬን፥ ቀሚሴንና መደረቢያዬን፥ ዘይቴንና የሚገባኝን ሁሉ የሚሰጡኝ ወዳጆችን እከተላቸው ዘንድ እሄዳለሁ” ብላለችና አሳፈረቻቸው።
እግዚአብሔርም፥ “የእስራኤል ልጆች ወደ ሌሎች አማልክት ቢመለሱና የዘቢብ ጥፍጥፍን ቢወድዱ እንኳን፥ እግዚአብሔር እንደሚወድዳቸው አንተም ክፋትና ዝሙት ያለባትን ሴት ውደድ” አለኝ።
እስራኤል ሆይ! ከአምላክህ ርቀህ አመንዝረሃልና እንደ አሕዛብ ደስ አይበልህ፤ ሐሴትንም አታድርግ፤ ከእህሉና ከወይኑ አውድማ ሁሉ ይልቅ የግልሙትና ዋጋን ወድደሃል።
የጽዮን ልጅ ሆይ፥ ቀንድሽን ብረት፥ ጥፍርሽንም ናስ አደርጋለሁና ተነሺ አሂጂ፥ ብዙ አሕዛብንም ታደቅቂአለሽ፥ ትርፋቸውንም ለእግዚአብሔር፥ ሀብታቸውንም ለምድር ሁሉ ጌታ ትቀድሻለሽ።
እነርሱ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ያይደለ ለሆዳቸው ይገዛሉና፤ በነገር ማታለልና በማለዛዘብም የብዙዎች የዋሃንን ልብ ያስታሉ፤