La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዕብራውያን 2:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ነገር ግን መጽ​ሐፍ እን​ዲህ ብሎ የመ​ሰ​ከ​ረ​በት ስፍራ አለ፤ “ታስ​በው ዘንድ ሰው ምን​ድን ነው? ትጐ​በ​ኘ​ውስ ዘንድ የሰው ልጅ ምን​ድን ነው?

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ነገር ግን አንዱ በሌላ ስፍራ እንዲህ ብሎ መስክሯል፤ “በሐሳብህ ስፍራ ትሰጠው ዘንድ ሰው ምንድን ነው? ትጠነቀቅለትም ዘንድ የሰው ልጅ ምንድን ነው?

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እንዲያውም በአንድ ስፍራ እንዲህ ተብሎ ተመስክሯል፦ “ታስበው ዘንድ ሰው ምንድነው? ወይስ ትጠነቀቅለት ዘንድ የሰው ልጅ ምንድነው?

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እንዲያውም በቅዱሳት መጻሕፍት በአንድ ስፍራ እንዲህ ተብሎአል፦ “አንተ እርሱን ታስበው ዘንድ ሰው ምንድን ነው? ለእርሱስ ትጠነቀቅለት ዘንድ የሰው ልጅ ምንድን ነው?

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ነገር ግን አንዱ በአንድ ስፍራ፦ ታስበው ዘንድ ሰው ምንድር ነው? ወይስ ትጎበኘው ዘንድ የሰው ልጅ ምንድር ነው?

Ver Capítulo



ዕብራውያን 2:6
16 Referencias Cruzadas  

ዮሴ​ፍም ወን​ድ​ሞ​ቹን አላ​ቸው፥ “እኔ እሞ​ታ​ለሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መጐ​ብ​ኘ​ትን ይጐ​በ​ኛ​ች​ኋል፤ ከዚ​ህ​ችም ምድር ያወ​ጣ​ች​ኋል። ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለይ​ስ​ሐቅ ለያ​ዕ​ቆ​ብም ወደ ማለ​ላ​ቸው ምድር ያገ​ባ​ች​ኋል።”


ንጹሕ ይሆን ዘንድ ሟች ሰው ማን ነው? ጻድ​ቅስ ይሆን ዘንድ ከሴት የተ​ወ​ለደ ማን ነው?


ይል​ቁ​ንስ ፈራሽ የሆነ ሰው፥ ትልም የሆነ የሰው ልጅ ምንኛ ያንስ!”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላቅ ነው፥ ምስ​ጋ​ና​ውም እጅግ ብዙ ነው፤ ለታ​ላ​ቅ​ነ​ቱም ዳርቻ የለ​ውም።


አሕ​ዛብ ሁሉ በፊቱ እን​ዳ​ል​ነ​በሩ ናቸው፤ እንደ ከንቱ ነገ​ርም ይመ​ስ​ላሉ።


እኔ ነኝ፤ የማ​ጽ​ና​ናሽ እኔ ነኝ፤ አንቺ እን​ግ​ዲህ ዕወቂ፤ ማንን ፈራሽ? የሚ​ሞ​ተ​ውን ሰው እንደ ሣርም የሚ​ጠ​ወ​ል​ገ​ውን የሰው ልጅ ነውን?


“ይቅር ያለን፥ ለወ​ገ​ኖ​ቹም ድኅ​ነ​ትን ያደ​ረገ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን፤


ከአ​ር​ያም በጐ​በ​ኘን በአ​ም​ላ​ካ​ችን በይ​ቅ​ር​ታ​ውና በቸ​ር​ነቱ።


ሁሉም ፈሩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አመ​ሰ​ገኑ፤ እን​ዲ​ህም አሉ፥ “ታላቅ ነቢይ ተነ​ሣ​ልን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝ​ቡን ጐብ​ኝ​ቶ​አ​ልና።”


አስቀድመን ደግሞ እንዳልናችሁና እንደ መሰከርንላችሁ፥ ጌታ ስለዚህ ነገር ሁሉ የሚበቀል ነውና፥ ማንም በዚህ ነገር አይተላለፍ፤ ወንድሙንም አያታልል።


ስለ ሰባ​ተ​ኛ​ውም ቀን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ከሥ​ራው ሁሉ ዐረፈ” ብሎ​አ​ልና።


ዳግ​መ​ኛም፥ “እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት የዘ​ለ​ዓ​ለም ካህን አንተ ነህ” ይላል።


በእነርሱም የነበረ የክርስቶስ መንፈስ፥ ስለ ክርስቶስ መከራ ከእርሱም በኋላ ስለሚመጣው ክብር አስቀድሞ እየመሰከረ፥ በምን ወይም እንዴት ባለ ዘመን እንዳመለከተ ይመረምሩ ነበር።