ዘፍጥረት 49:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብርሃምንና ሚስቱ ሣራንም በዚያ ቀበሩአቸው፤ ይስሐቅንና ሚስቱ ርብቃንም በዚያ ቀበሩአቸው፤ ከዚያም እኔ ልያን ቀበርኋት አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ አብርሃምና ሚስቱ ሣራ ተቀብረዋል፤ በዚያ ይሥሐቅና ሚስቱ ርብቃ ተቀብረዋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አብርሃምና ሚስቱ ሣራ ከዚያ ተቀበሩ፥ ይስሐቅና ሚስቱ ርብቃ ከዚያ ተቀበሩ፥ ከዚያም እኔ ልያን ቀበርኋት፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አብርሃምና ሚስቱ ሣራ፥ ይስሐቅና ሚስቱም ርብቃ የተቀበሩት እዚያ ነው፤ እኔም ልያን የቀበርኳት እዚያው ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አብርሃምና ሚስቱ ሣራ ከዚያ ተቀበሩ ይስሐቅና ሚስቱ ርብቃ ከዚያ ተቀበሩ ከዚያም እኔ ልያን ቀበርኍት፤ |
ልጆቹ ይስሐቅና ይስማኤልም በመምሬ ፊት ለፊት ባለው በኬጢያዊው በሰዓር ልጅ በኤፍሮን እርሻ ላይ ባለ ድርብ ክፍል በሆነው ዋሻ ውስጥ ቀበሩት።
ከአባቶችም ጋር በአንቀላፋሁ ጊዜ ከግብፅ ምድር አውጥተህ ትወስደኛለህ፤ በአባቶችም መቃብር ትቀብረኛለህ።” እርሱም፥ “እንደ ቃልህ አደርጋለሁ” አለ። እርሱም፥ “ማልልኝ” አለው።
ልጆቹም ወደ ከነዓን ምድር መለሱት፤ ባለ ሁለት ክፍል በሆነች ዋሻም ቀበሩት፤ እርስዋም በመምሬ ፊት ያለች፥ አብርሃም ለመቃብር ርስት ከኬጢያዊው ከኤፍሮን ከእርሻው ጋር የገዛት ዋሻ ናት።