ዘፍጥረት 49:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምክራቸው የሰደቡት ጌቶች ሆኑበት፤ ቀስተኞችም ወጉት፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀስተኞች በጭካኔ አጠቁት፤ በጥላቻም ነደፉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቀስተኞች አስቸገሩት፥ ነደፉትም፥ ተቃወሙትም፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀስተኞቹ በብርቱ ያጠቁታል፤ በቀስታቸውም እየነደፉ ያሳድዱታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቀስተኞች አስቸገሩት ነደፋትም ተቃወሙትም ነገር ግም ቀስቱ እንደ ጸና ቀረ፤ |
እነዚያ ይስማኤላውያን ነጋዴዎችም ሲያልፉ ወንድሞቹ ዮሴፍን ከጕድጓድ ጐትተው አወጡት፤ ለይስማኤላውያንም ዮሴፍን በሃያ ብር ሸጡት፤ እነርሱም ዮሴፍን ወደ ግብፅ ወሰዱት።
እነርሱም እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፥ “በእውነት ወንድማችንን በድለናል፤ እኛን በመማጠን ነፍሱ ስትጨነቅ አይተን አልሰማነውምና፤ ስለዚህ ይህ መከራ መጣብን።”
“ዮሴፍ የሚያድግ ልጅ ነው፤ ለእኔ በጣም የተወደደ የሚቀናልኝና የሚያድግልኝ ልጅ ነው፤ ወደ እኔ የሚመለስም ጐልማሳ ነው።
ነገር ግን ቀስቶቻቸው በኀይል ተቀጠቀጡ፤ የእጆቻቸው ክንድ ሥርም በያዕቆብ ኀያል እጅ ዛለ፤ በዚያም በአባትህ አምላክ ዘንድ እስራኤልን አጸናው።
በእኔም ሰላምን እንድታገኙ ይህን ነገርኋችሁ፤ በዓለም ግን መከራን ትቀበላላችሁ፤ ነገር ግን ጽኑ፤ እኔ ዓለሙን ድል ነሥቼዋለሁና።”
የደቀ መዛሙርትንም ልቡና አጽናኑ፤ በሃይማኖትም እንዲጸኑ፦“ በብዙ ድካምና መከራ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት እንገባ ዘንድ ይገባናል” እያሉ መከሩአቸው።