ዘፍጥረት 34:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የያዕቆብም ልጆች ለሴኬምና ለአባቱ ለኤሞር በተንኰል መለሱ፤ እኅታቸውን ዲናን አስነውሮአታልና፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የያዕቆብ ወንዶች ልጆችም፣ በእኅታቸው በዲና ላይ ስለ ተፈጸመው ነውር፣ የሆዳቸውን በሆዳቸው ይዘው፣ ለሴኬምና ለአባቱ ለኤሞር በተንኰል መልስ ሰጡ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የያዕቆብም ልጆች፥ እኅታቸውን ዲናን አርክሶአታልና፥ ለሴኬምና ለአባቱ ለኤሞር በተንኰል መለሱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሴኬም እኅታቸውን ዲናን አስነውሮ ስለ ነበር የያዕቆብ ልጆች ለእርሱና ለአባቱ ለሐሞር በተንኰል እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የያዕቆብም ልጆች ለሴኬምና ለአባቱ ለኤሞር በተንኮል መለሱ እኅታቸውን ዲናን አርክሶአታልና፤ |
የዲና ወንድሞች ስምዖንና ሌዊም እንዲህ አሉአቸው፥ “እኅታችንን ላልተገረዘ ሰው ለመስጠት ይህን ነገር እናደርግ ዘንድ አይቻለንም፤ ይህ ነውር ይሆንብናልና።
ኀጢአተኛ ሰው በከንፈሩ ኀጢአት ወደ ወጥመድ ይወድቃል፤ ጻድቅ ግን ከእርሱ ያመልጣል። አስፍቶ የሚመለከት ሰው ብዙ ምሕረትን ያገኛል። ድንገት በበር የሚገናኝ ግን ነፍሳትን ያስጨንቃል።
በድለናል፤ ዋሽተናልም፤ አምላካችንንም መከተል ትተናል፤ ዐመፃን ተናግረናል፤ ከድተንሃልም፤ የኀጢአትንም ቃል ፀንሰን፤ ከልብ አውጥተናል።
ወንድሞቻችን፥ ራሳችሁ አትበቀሉ፤ ቍጣን አሳልፏት፥ “እኔ እበቀላለሁ፤ እኔ ብድራትን እከፍላለሁ ይላል እግዚአብሔር” ተብሎ ተጽፎአልና።