Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢዮብ 13:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 እና​ንተ ግን የዐ​መፅ ባለ መድ​ኀ​ኒ​ቶች፥ ሁላ​ች​ሁም የክ​ፋት ፈዋ​ሾች ናችሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 እናንተ ግን፣ በሐሰት የምትለብጡ ናችሁ፤ ሁላችሁ የማትረቡ ሐኪሞች ሆናችኋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 እናንተ ግን በሐሰት ለባጮች ናችሁ፥ ሁላችሁም የማትጠቅሙ ሐኪሞች ናችሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 እናንተ ግን በሐሰት የተሞላችሁ ናችሁ፤ ማንንም መፈወስ እንደማይችሉ ሐኪሞች ናችሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 እናንተ ግን በሐሰት ለባጮች ናችሁ፥ ሁላችሁ የማትጠቅሙ ባለ መድኃኒቶች ናችሁ።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 13:4
23 Referencias Cruzadas  

እኔም፥ “አንተ ከል​ብህ ፈጥ​ረ​ኸ​ዋል እንጂ እንደ ተና​ገ​ር​ኸው ነገር አይ​ደ​ለም” ብዬ ላክ​ሁ​በት።


“እን​ደ​ዚህ ያለ ብዙ ነገር ሰማሁ፤ እና​ንተ ሁላ​ችሁ የም​ታ​ደ​ክሙ አጽ​ና​ኞች ናችሁ።


እነሆ፥ ሁላ​ች​ሁም፥ በክ​ፉ​ዎች ላይ ክፋት እን​ደ​ም​ት​መ​ጣ​ባ​ቸው ታው​ቃ​ላ​ችሁ።


“ወን​ድ​ሞ​ቼም እንደ ደረቅ ወንዝ፥ እንደ አለፈ ማዕ​በ​ልም አላ​ወ​ቁ​ኝም።


በከ​ተ​ሞ​ችና በገ​ን​ዘ​ቦች የሚ​ታ​መኑ ያፍ​ራሉ።


አሁ​ንም እና​ንተ ያለ ምሕ​ረት መጣ​ችሁ፤ ቍስ​ሌ​ንም አይ​ታ​ችሁ ፈራ​ችሁ።


“በባ​ል​ን​ጀ​ራህ ላይ በሐ​ሰት አት​መ​ስ​ክር።


እነሆ ሐሰ​ትን በሚ​ያ​ልሙ፥ በሚ​ና​ገ​ሩም፥ በሐ​ሰ​ታ​ቸ​ውና በድ​ፍ​ረ​ታ​ቸ​ውም ሕዝ​ቤን በሚ​ያ​ስቱ በነ​ቢ​ያት ላይ ነኝ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እኔም አል​ላ​ክ​ኋ​ቸ​ውም፤ አላ​ዘ​ዝ​ኋ​ቸ​ው​ምም፤ ለእ​ነ​ዚህ ሕዝብ በማ​ና​ቸ​ውም አይ​ረ​ቡ​አ​ቸ​ውም፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ትጠ​ገን ዘንድ ክር​ክ​ር​ህን የሚ​ፈ​ር​ድ​ልህ ሰው የለም፤ ቍስ​ል​ህ​ንም የሚ​ፈ​ውስ መድ​ኀ​ኒት የለ​ህም።


ድን​ግ​ሊቱ የግ​ብፅ ልጅ ሆይ! ወደ ገለ​ዓድ ውጪ፤ የሚ​ቀባ መድ​ኀ​ኒ​ት​ንም ውሰጂ፤ ለም​ንም የማ​ይ​ጠ​ቅ​ም​ሽን መድ​ኀ​ኒት በከ​ንቱ አብ​ዝ​ተ​ሻል።


የሕ​ዝ​ቤ​ንም ስብ​ራት በጥ​ቂቱ ይፈ​ው​ሳሉ፤ ሰላም ሳይ​ሆን፦ ሰላም ሰላም ይላሉ።


በገ​ለ​ዓድ መድ​ኀ​ኒት የለ​ምን? ወይስ በዚያ ሐኪም የለ​ምን? የወ​ገኔ ሴት ልጅ ፈውስ ስለ ምን አል​ሆ​ነም?


የደ​ከ​መ​ውን አላ​ጸ​ና​ች​ሁ​ትም፤ የታ​መ​መ​ው​ንም አል​ፈ​ወ​ሳ​ች​ሁ​ትም፤ የተ​ሰ​በ​ረ​ው​ንም አል​ጠ​ገ​ና​ች​ሁ​ትም፤ የባ​ዘ​ነ​ው​ንም አል​መ​ለ​ሳ​ች​ሁ​ትም፤ የጠ​ፋ​ው​ንም አል​ፈ​ለ​ጋ​ች​ሁ​ትም፤ በኀ​ይ​ልና በጭ​ቈ​ናም ገዛ​ች​ኋ​ቸው።


ኤፍ​ሬ​ምም ደዌ​ውን አያት፤ ይሁ​ዳም ሥቃ​ዩን አያት፤ ኤፍ​ሬም ወደ አሦር ሄደ፤ ወደ ንጉ​ሡም ወደ ኢያ​ሪም መል​እ​ክ​ተ​ኛን ላከ፤ እርሱ ግን ፈጽሞ ይፈ​ው​ሳ​ችሁ ዘንድ አል​ቻ​ለም፤ ከእ​ና​ን​ተም ሕማም አል​ተ​ወ​ገ​ደም።


ኢየሱስም ሰምቶ “ሕመምተኞች እንጂ ብርቱዎች ባለ መድኃኒት አያስፈልጋቸውም፤ ኀጢአተኞችን እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁም፤” አላቸው።


ከብዙ ባለ መድኃኒቶችም ብዙ ተሠቃየች፤ ገንዘብዋንም ሁሉ ከስራ ባሰባት እንጂ ምንም አልተጠቀመችም፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos