La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 33:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዔሳ​ውም ዐይ​ኑን አነ​ሣና ሴቶ​ች​ንና ልጆ​ችን አየ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “እነ​ዚህ ምኖ​ችህ ናቸው?” እር​ሱም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእኔ ለአ​ገ​ል​ጋ​ይህ የሰ​ጠኝ ልጆች ናቸው” አለ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም ዔሳው ቀና ብሎ ሲመለከት ሴቶቹንና ልጆቹን አየ፤ እርሱም፣ “እነዚህ ዐብረውህ ያሉት እነማን ናቸው?” ብሎ ጠየቀው። ያዕቆብም መልሶ፣ “እነዚህማ እግዚአብሔር በቸርነቱ ለእኔ ለአገልጋይህ የሰጠኝ ልጆች ናቸው” አለው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዓይኑን አንስቶም ሴቶችንና ልጆችን ባየ ጊዜ፥ “እነዚህ ምኖችህ ናቸው?” አለ። እርሱም፦ “እግዚአብሔር ለእኔ ለአገልጋይህ የሰጠኝ ልጆች ናቸው” አለ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ዔሳው በዙሪያው ተመልክቶ ሴቶቹንና ልጆቹን ባየ ጊዜ “እነዚህ ሁሉ ከአንተ ጋር ያሉ ሰዎች የማን ናቸው?” አለ። ያዕቆብም “ጌታዬ ሆይ፥ እነዚህ እግዚአብሔር በቸርነቱ የሰጠኝ ልጆች ናቸው” ሲል መለሰ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዓይኑንም አነሣና ሴቶችንና ልጆችን አየ እንዲህም አለ፦ እነዚህ ምኖችህ ናቸው? እርሱም፦ እግዚአብሔር ለእኔ ለባሪያህ የሰጠኝ ልጆች ናቸው አለ።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 33:5
9 Referencias Cruzadas  

ያዕ​ቆ​ብም፥ “የማ​ኅ​ፀ​ን​ሽን ፍሬ የም​ከ​ለ​ክ​ልሽ እኔ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝን?” ብሎ ራሔ​ልን ተቈ​ጣት።


ዕቁ​ባ​ቶ​ቹም ከል​ጆ​ቻ​ቸው ጋር ቀር​በው ሰገዱ፤


ዮሴ​ፍም ለአ​ባቱ ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚህ የሰ​ጠኝ ልጆች ናቸው” አለው። ያዕ​ቆ​ብም፥ “እባ​ር​ካ​ቸው ዘንድ ወደ እኔ አቅ​ር​ብ​ልኝ” አለው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ብዙ ልጆች ሰጥ​ቶ​ኛ​ልና ከል​ጆቼ ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት ዙፋን ላይ ተቀ​ምጦ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ይነ​ግሥ ዘንድ ልጄን ሰሎ​ሞ​ንን መር​ጦ​ታል።


ሚስ​ትህ በቤ​ትህ እል​ፍኝ ውስጥ እን​ደ​ሚ​ያ​ፈራ ወይን ትሆ​ና​ለች፤ ልጆ​ች​ህም በማ​ዕ​ድህ ዙሪያ እንደ አዲስ የወ​ይራ ተክል ይሆ​ናሉ።


እነሆ፥ እኔና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ጠኝ ልጆች ለእ​ስ​ራ​ኤል በጽ​ዮን ተራራ ከሚ​ኖ​ረው ከሠ​ራ​ዊት ጌታ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ምል​ክ​ትና ተአ​ም​ራት ነን።


ዳግ​መ​ኛም፥ “እኔና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ጠኝ ልጆች እነሆ፥” አለ፤ ዳግ​መ​ኛም፥ “እኔ እታ​መ​ን​በ​ታ​ለሁ” አለ።


ቦዔዝም ሩትን ወሰደ፥ ሚስትም ሆነችው፣ ደረሰባትም፥ እግዚአብሔርም ፅንስ ለጣት፥ ወንድ ልጅም ወለደች።


ስለ​ዚህ ልጅ ተሳ​ልሁ፤ ጸለ​ይ​ሁም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የለ​መ​ን​ሁ​ትን ልመ​ና​ዬን ሰጥ​ቶ​ኛል፤