እንደዚህ በልቡ ያሰበውን መናገሩን ሳይፈጽም እንዲህ ሆነ፦ የአብርሃም ወንድም የናኮር ሚስት የሚልካ ልጅ የባቱኤል ሴት ልጅ ርብቃ እነሆ፥ መጣች፥ እንስራዋንም በጫንቃዋ ተሸክማ ነበር።
ዘፍጥረት 24:50 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባቱኤልና ላባም መለሱ፤ እንዲህም አሉ፥ “ነገሩ ከእግዚአብሔር ዘንድ መጥቶአል፤ ክፉ ወይም በጎ ልንመልስልህ አንችልም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ላባና ባቱኤል እንዲህ ሲሉ መለሱ፤ “ነገሩ ከእግዚአብሔር ስለ ሆነ በዚህም ሆነ በዚያ ምንም ማለት አንችልም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ላባና ባቱኤልም መለሱ እንዲህም አሉ፦ “ነገሩ ከእግዚአብሔር ዘንድ መጥቷል ክፉም በጎም ልንመልስልህ አንችልም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ላባና ባቱኤልም “ይህ ነገር ከእግዚአብሔር የመጣ ስለ ሆነ፥ መከልከል አንችልም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ላባና ባቱኤልም መለሱ እንዲህም አሉ፦ ነገሩ ከእግዚአብሔር ዘንድ መጥቶአል ክፉም በጎ፥ ልንመልስልህ አንችልም |
እንደዚህ በልቡ ያሰበውን መናገሩን ሳይፈጽም እንዲህ ሆነ፦ የአብርሃም ወንድም የናኮር ሚስት የሚልካ ልጅ የባቱኤል ሴት ልጅ ርብቃ እነሆ፥ መጣች፥ እንስራዋንም በጫንቃዋ ተሸክማ ነበር።
እኅታቸው ርብቃንም መረቁአትና፥ “አንቺ እኅታችን፥ እልፍ አእላፋት ሁኚ፤ ዘርሽም የጠላት ሀገሮችን ይውረስ” አሉአት።
እግዚአብሔርም ወደ ሶርያዊው ወደ ላባ በሌሊት በሕልም መጥቶ፥ “በባሪያዬ በያዕቆብ ላይ ክፉ ነገር እንዳትናገር ተጠንቀቅ” አለው።
አሁንም በአንተ ላይ ክፉ ማድረግ በቻልሁ ነበር፤ ነገር ግን የአባትህ አምላክ ትናንት፦ በያዕቆብ ላይ ክፉ እንዳታደርግ ተጠንቀቅ ብሎ ነገረኝ።
አቤሴሎምም አምኖንን ክፉም ሆነ መልካም አልተናገረውም። እኅቱን ትዕማርን ስላስነወራት አቤሴሎም አምኖንን ጠልቶታልና።
እግዚአብሔርም በሴሎናዊው በአኪያ አፍ ለናባጥ ልጅ ለኢዮርብዓም የተናገረውን ነገር እንዲያጸና ለውጡ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነበርና ንጉሡ ሕዝቡን አልሰማም።
“እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ይህ ነገር ከእኔ ዘንድ ነውና አትውጡ፤ የእስራኤልንም ልጆች ወንድሞቻችሁን አትውጉ፤ እያንዳንዱም ወደ ቤቱ ይመለስ።” እነርሱም የእግዚአብሔርን ቃል ሰሙ፤ እንደ እግዚአብሔርም ቃል ተመልሰው ሄዱ።
ኢየሱስ እንዲህ አላቸው “ ‘ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ፤ ይህም ከጌታ ዘንድ ሆነ፤ ለዐይኖቻችንም ድንቅ ነው፤’ የሚለውን ከቶ በመጽሐፍ አላነበባችሁምን?
እንግዲህ እግዚአብሔር በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ለአመንነው ለእኛ እንደ ሰጠን፥ ያን ጸጋውን እንደ እኛ አስተካክሎ ከሰጣቸው እግዚአብሔርን ልከለክል የምችል እኔ ማነኝ?”