Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ነገሥት 12:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ይህ ነገር ከእኔ ዘንድ ነውና አት​ውጡ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን አት​ውጉ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ወደ ቤቱ ይመ​ለስ።” እነ​ር​ሱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ሰሙ፤ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ተመ​ል​ሰው ሄዱ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ‘እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፤ ይህ ነገር ከእኔ የሆነ ነውና ወንድሞቻችሁን እስራኤላውያንን ለመውጋት አትውጡ፤ እያንዳንዳችሁ ወደየቤታችሁ ተመለሱ።’ ” ስለዚህ እግዚአብሔር እንዳዘዘው የእግዚአብሔርን ቃል ሰሙ፤ ወደየቤታቸውም ተመለሱ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 “ወንድሞቻችሁ በሆኑት በእስራኤላውያን ላይ አደጋ አትጣሉ፤ ሁላችሁም ወደየቤታችሁ ሂዱ፤ ይህ የሆነውም በእኔ ፈቃድ ነው” ብሎ እንዲነግር አዘዘው። እነርሱም ሁሉ ለጌታ ቃል ታዛዦች በመሆን ወደየቤታቸው ተመልሰው ሄዱ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 “ወንድሞቻችሁ በሆኑት በእስራኤላውያን ላይ አደጋ አትጣሉ፤ ሁላችሁም ወደየቤታችሁ ሂዱ፤ ይህ የሆነው በእኔ ፈቃድ ነው” ብሎ እንዲነግር አዘዘው። እነርሱም ሁሉ ለእግዚአብሔር ቃል ታዛዦች በመሆን ወደየቤታቸው ተመልሰው ሄዱ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ‘ይህ ነገር ከእኔ ዘንድ ነውና አትውጡ፤ የእስራኤልንም ልጆች ወንድሞቻችሁን አትውጉ፤ እያንዳንዱም ወደ ቤቱ ይመለስ፤’ ብለህ ንገራቸው፤” ሲል መጣ። የእግዚአብሔርንም ቃል ሰሙ፤ እንደ እግዚአብሔርም ቃል ተመልሰው ሄዱ።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 12:24
13 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሴ​ሎ​ና​ዊው በአ​ኪያ አፍ ለና​ባጥ ልጅ ለኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም የተ​ና​ገ​ረ​ውን ነገር እን​ዲ​ያ​ጸና ለውጡ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ነበ​ርና ንጉሡ ሕዝ​ቡን አል​ሰ​ማም።


ራሳ​ቸ​ውን አነ​ገሡ፤ ከእ​ኔም ዘንድ አይ​ደ​ለም፤ አለ​ቆ​ች​ንም አደ​ረጉ፤ እኔም አላ​ወ​ቅ​ሁም፤ ለጥ​ፋ​ታ​ቸ​ውም ከብ​ራ​ቸ​ውና ከወ​ር​ቃ​ቸው ጣዖ​ታ​ትን ለራ​ሳ​ቸው አደ​ረጉ።


ንጉሡ አሜ​ስ​ያ​ስም ከኤ​ፍ​ሬም ከተ​ሞች የመጡ ጭፍ​ሮች ወደ ስፍ​ራ​ቸው ይመ​ለሱ ዘንድ ለይቶ አሰ​ና​በ​ታ​ቸው፤ ስለ​ዚ​ህም ቍጣ​ቸው በይ​ሁዳ ላይ ጸና፤ ወደ ስፍ​ራ​ቸ​ውም በጽኑ ቍጣ ተመ​ለሱ።


‘እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ይህ ነገር ከእኔ ዘንድ ነውና አት​ውጡ፤ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁ​ንም አት​ውጉ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ወደ ቤቱ ይመ​ለስ’ ብለህ ንገ​ራ​ቸው።” የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል ሰሙ፤ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓ​ምም ላይ ከመ​ሄድ ተመ​ለሱ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ና​ንተ ጋር አይ​ደ​ለ​ምና በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችሁ ፊት እን​ዳ​ት​ወ​ድቁ አት​ውጡ።


ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም በተ​ራ​ራ​ማው በኤ​ፍ​ሬም ሀገር ሰቂ​ማን ሠርቶ በዚያ ተቀ​መጠ፤ ደግ​ሞም ከዚያ ወጥቶ ፋኑ​ኤ​ልን ሠራ።


ባቱ​ኤ​ልና ላባም መለሱ፤ እን​ዲ​ህም አሉ፥ “ነገሩ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ መጥ​ቶ​አል፤ ክፉ ወይም በጎ ልን​መ​ል​ስ​ልህ አን​ች​ልም።


አባ​ቱና እና​ቱም ነገሩ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆነ አላ​ወ​ቁም፤ እርሱ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን በቀ​ልን ይመ​ልስ ዘንድ ይፈ​ልግ ነበ​ርና። በዚ​ያም ወራት ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እስ​ራ​ኤ​ልን ይገዙ ነበር።


በዘ​መ​ኑም ሁሉ በሮ​ብ​ዓ​ምና በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም መካ​ከል ጦር​ነት ነበረ።


ወደ ኢዮ​ራም በመ​ም​ጣ​ቱም የአ​ካ​ዝ​ያስ ጥፋት ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆነ፤ በመ​ጣም ጊዜ ከኢ​ዮ​ራም ጋር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የአ​ክ​ዓ​ብን ቤት ያጠፋ ዘንድ ወደ ቀባው ወደ ናሚሲ ልጅ ወደ ኢዩ ወጣ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios