La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዕዝራ 7:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከካ​ህ​ና​ቱም፥ ከሌ​ዋ​ው​ያ​ኑም፥ ከመ​ዘ​ም​ራ​ኑም፥ ከበ​ረ​ኞ​ቹም፥ ከና​ታ​ኒ​ምም በን​ጉሡ በአ​ር​ተ​ሰ​ስታ በሰ​ባ​ተ​ኛው ዓመት ዐያ​ሌ​ዎች ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወጡ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እንደዚሁም አንዳንድ እስራኤላውያን፣ ከካህናት፣ ከሌዋውያን፣ ከመዘምራን፣ ከበር ጠባቂዎችና ከቤተ መቅደሱ አገልጋዮች ጋራ በመሆን በንጉሡ በአርጤክስስ ዘመነ መንግሥት በሰባተኛው ዓመት ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በንጉሡ በአርጤክስስ በሰባተኛው ዓመት ከእስራኤል ልጆች አንዳንዶቹ፥ ከካህናቱም አንዳንዶቹ፥ ሌዋውያኑ፥ መዘምራኑ፥ በር ጠባቂዎቹና፥ የቤተ መቅደስ አገልጋዮቹ ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እንዲሁም ንጉሥ አርጤክስስ በነገሠ በሰባተኛው ዓመት ከእስራኤል ልጆች መካከል ካህናት፥ ሌዋውያን፥ መዘምራን፥ በር ጠባቂዎችና የቤተ መቅደስ አገልጋዮች ከዕዝራ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከእስራኤልም ልጆች ከካህናቱ፥ ከሌዋውያኑ፥ ከመዘምራኑ፥ ከበረኞቹና ከናታኒም በንጉሡ በአርጤክስስ በሰባተኛው ዓመት አያሌዎች ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ።

Ver Capítulo



ዕዝራ 7:7
14 Referencias Cruzadas  

የአ​ይ​ሁድ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና ሌዋ​ው​ያ​ንም በነ​ቢዩ በሐ​ጌና በአዶ ልጅ በዘ​ካ​ር​ያስ ትን​ቢት መሠ​ረት ሠሩ፤ ተከ​ና​ወ​ነ​ላ​ቸ​ውም። እንደ እስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ትእ​ዛዝ፥ እንደ ፋር​ስም ነገ​ሥ​ታት እንደ ቂሮ​ስና እንደ ዳር​ዮስ፥ እንደ አር​ተ​ሰ​ስ​ታም ትእ​ዛዝ ሠር​ተው ፈጸሙ።


ደግ​ሞም በካ​ህ​ና​ቱና በሌ​ዋ​ው​ያኑ፥ በመ​ዘ​ም​ራ​ኑም፥ በበ​ረ​ኞ​ቹም፥ በና​ታ​ኒ​ምም በዚ​ህም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በሚ​ሠሩ አገ​ል​ጋ​ዮች ላይ ግብ​ርና ቀረጥ እን​ዳ​ይ​ጣል፥ የም​ት​ገ​ዙ​አ​ቸ​ውም አገ​ዛዝ እን​ዳ​ይ​ኖር ብለን እና​ስ​ታ​ው​ቃ​ች​ኋ​ለን።


በን​ጉ​ሡም በሰ​ባ​ተ​ኛው ዓመት በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ወር ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ደረሱ።


የኬ​ል​ቅያ ልጅ የነ​ህ​ምያ ቃል። በሃ​ያ​ኛው ዓመት በካ​ሴሎ ወር እን​ዲህ ሆነ፤ እኔ በሱሳ ግንብ ሳለሁ፥


የቀ​ሩ​ትም ሕዝብ፥ ካህ​ና​ቱም፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑም፥ በረ​ኞ​ቹም፥ መዘ​ም​ራ​ንም፥ ናታ​ኒ​ምም፥ ከም​ድ​ርም አሕ​ዛብ ራሳ​ቸ​ውን የለ​ዩና ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ የገቡ ሁሉ፥ ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም፥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውም፥ የሚ​ያ​ው​ቁ​ትና የሚ​ያ​ስ​ተ​ው​ሉ​ትም ሁሉ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ው​ንና ታላ​ላ​ቆ​ቻ​ቸ​ውን አበ​ረ​ታቱ፤


ከሰ​ላ​ት​ያል ልጅ ከዘ​ሩ​ባ​ቤ​ልና ከኢ​ያሱ ጋር የወ​ጡት ካህ​ና​ትና ሌዋ​ው​ያን እነ​ዚህ ነበሩ፤ ሠራ​ህያ፥ ኤር​ም​ያስ፥ ዔዝራ፤


በን​ጉሡ በአ​ር​ተ​ሰ​ስታ በሃ​ያ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት በኔ​ሳን ወር የወ​ይን ጠጅ በፊቱ ነበር፤ ጠጁ​ንም አን​ሥቼ ለን​ጉሡ ሰጠ​ሁት። በፊ​ቱም ሌላ ሰው አል​ነ​በ​ረም።