Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ነህምያ 2:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 በን​ጉሡ በአ​ር​ተ​ሰ​ስታ በሃ​ያ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት በኔ​ሳን ወር የወ​ይን ጠጅ በፊቱ ነበር፤ ጠጁ​ንም አን​ሥቼ ለን​ጉሡ ሰጠ​ሁት። በፊ​ቱም ሌላ ሰው አል​ነ​በ​ረም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 በንጉሡ በአርጤክስስ ዘመነ መንግሥት በሃያኛው ዓመት ኒሳን ተብሎ በሚጠራው ወር የወይን ጠጅ በመጣለት ጊዜ፣ የወይን ጠጁን አንሥቼ ለንጉሡ ሰጠሁት። ቀድሞ በፊቱ ዐዝኜ አላውቅም ነበር፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 እንዲህም ሆነ በንጉሡ አርታሕሻስት በሀያኛው ዓመት በኒሳን ወር፥ የወይን ጠጅ በፊቱ ነበረ፥ የወይን ጠጁን አንሥቼ ለንጉሡ ሰጠሁት። ከዚህ ቀደም በፊቱ አዝኜ አላውቅም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 አርጤክስስ በነገሠ በሃያኛው ዓመት ኒሳን ተብሎ በሚጠራው ወር ከዕለታት በአንዱ ቀን ለንጉሠ ነገሥቱ የወይን ጠጅ አቀረብኩለት፤ ከዚያች ቀን በቀር ከዚህ ቀደም በፊቴ ላይ ምንም ዐይነት የሐዘን ምልክት አይቶብኝ አያውቅም ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 በንጉሡ በአርጤክስስ በሀያኛው ዓመት በኒሳን ወር የወይን ጠጅ በፊቱ በነበረ ጊዜ ጠጁን አንሥቼ ለንጉሡ ሰጠሁት። ቀድሞ ግን በፊቱ ያለ ኃዘን እኖር ነበር።

Ver Capítulo Copiar




ነህምያ 2:1
9 Referencias Cruzadas  

ከዚ​ህም ነገር በኋላ በፋ​ርስ ንጉሥ በአ​ር​ተ​ሰ​ስታ መን​ግ​ሥት ዕዝራ የሠ​ራያ ልጅ፥ የዓ​ዛ​ር​ያስ ልጅ፥ የኬ​ል​ቅ​ያስ ልጅ፥


ጌታ ሆይ፥ ጆሮህ የባ​ሪ​ያ​ህን ጸሎት፥ ስም​ህ​ንም ይፈሩ ዘንድ የሚ​ወ​ድ​ዱ​ትን የባ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ህን ጸሎት ያድ​ምጥ፤ ዛሬም ለባ​ሪ​ያህ አከ​ና​ው​ን​ለት፤ በዚ​ህም ሰው ፊት ምሕ​ረ​ትን ስጠው።” እኔም ለን​ጉሡ ጠጅ አሳ​ላፊ ነበ​ርሁ።


የኬ​ል​ቅያ ልጅ የነ​ህ​ምያ ቃል። በሃ​ያ​ኛው ዓመት በካ​ሴሎ ወር እን​ዲህ ሆነ፤ እኔ በሱሳ ግንብ ሳለሁ፥


ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከካ​ህ​ና​ቱም፥ ከሌ​ዋ​ው​ያ​ኑም፥ ከመ​ዘ​ም​ራ​ኑም፥ ከበ​ረ​ኞ​ቹም፥ ከና​ታ​ኒ​ምም በን​ጉሡ በአ​ር​ተ​ሰ​ስታ በሰ​ባ​ተ​ኛው ዓመት ዐያ​ሌ​ዎች ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወጡ።


የጠጅ አሳ​ላ​ፊ​ዎ​ቹ​ንም አለቃ ወደ ሹመቱ መለ​ሰው፤ ጽዋ​ው​ንም በፈ​ር​ዖን እጅ ሰጠ፤


የፈ​ር​ዖ​ንም ጽዋ በእጄ ነበር፤ ፍሬ​ው​ንም ወስጄ በፈ​ር​ዖን ጽዋ ጨመ​ቅ​ሁት፤ ጽዋ​ዉ​ንም ለፈ​ር​ዖን በእጁ ሰጠ​ሁት።”


በአ​ር​ተ​ሰ​ስታ ዘመን በሴ​ሌም፥ ሜት​ሪ​ዳጡ፥ ጣብ​ሄል፥ የቀ​ሩት ተባ​ባ​ሪ​ው​ቻ​ቸ​ውም ለፋ​ርስ ንጉሥ ለአ​ር​ተ​ሰ​ስታ ጻፉ፤ ደብ​ዳ​ቤ​ውም በሶ​ርያ ፊደ​ልና በሶ​ርያ ቋንቋ ተጽፎ ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios