ዘፀአት 22:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰው ከባልንጀራው አንዳች ቢዋስ ባለቤቱ ከእርሱ ጋር ሳይኖር ቢጎዳ፥ ወይም ቢሞት፥ ወይም ቢነጠቅ ፈጽሞ ይክፈለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አንድ ሰው ከጎረቤቱ እንስሳ ተውሶ ሳለ፣ ባለቤቱ በሌለበት ቢጐዳ ወይም ቢሞት ካሳ መክፈል አለበት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባለቤቱ ግን ከእርሱ ጋር ቢኖር አይክፈል፤ አከራይቶት ከሆነም ኪራዩን ብቻ ይክፈል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አንድ ሰው ከሌላው ሰው እንስሳ በውሰት ወስዶ ባለቤቱ በሌለበት እንስሳው ቢሞት ወይም ቢሰበር በውሰት ለሰጠው ሰው ካሳ ይክፈል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከባልንጀራው አንዳች ቢዋስ ባለቤቱ ከእርሱ ጋር ሳይኖር ቢጎዳ፥ ወይም ቢሞት፥ ፈጽሞ ይክፈለው። |
በባልንጀራው ከብት ላይ እጁን እንዳልዘረጋ የእግዚአብሔር መሐላ በሁለታቸው መካከል ይሁን፤ የከብቱም ባለቤት ይህን ከተቀበለ፥ እርሱ ምንም አይክፈል።
አሁንም ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ መልካምም አድርጉላቸው፤ እንዲመልሱላችሁ ተስፋ ሳታደርጉ አበድሩ፤ ዋጋችሁም ብዙ ይሆናል፤ የልዑልም ልጆች ትሆናላችሁ፤ እርሱ ለበጎዎችና ለክፉዎች ቸር ነውና።
ለምሕረቱም የሚገባ ትእዛዝ ይህ ነው፤ ባልንጀራህ ወይም ወንድምህ የሚከፍልህን ገንዘብ ሁሉ አትከፈል፤ የአምላክህ የእግዚአብሔር ምሕረት ተብላለችና።