Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 22:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 “አንድ ሰው ከሌላው ሰው እንስሳ በውሰት ወስዶ ባለቤቱ በሌለበት እንስሳው ቢሞት ወይም ቢሰበር በውሰት ለሰጠው ሰው ካሳ ይክፈል፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 “አንድ ሰው ከጎረቤቱ እንስሳ ተውሶ ሳለ፣ ባለቤቱ በሌለበት ቢጐዳ ወይም ቢሞት ካሳ መክፈል አለበት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ባለቤቱ ግን ከእርሱ ጋር ቢኖር አይክፈል፤ አከራይቶት ከሆነም ኪራዩን ብቻ ይክፈል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ሰው ከባ​ል​ን​ጀ​ራው አን​ዳች ቢዋስ ባለ​ቤቱ ከእ​ርሱ ጋር ሳይ​ኖር ቢጎዳ፥ ወይም ቢሞት፥ ወይም ቢነ​ጠቅ ፈጽሞ ይክ​ፈ​ለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ከባልንጀራው አንዳች ቢዋስ ባለቤቱ ከእርሱ ጋር ሳይኖር ቢጎዳ፥ ወይም ቢሞት፥ ፈጽሞ ይክፈለው።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 22:14
11 Referencias Cruzadas  

ሌሎችም ደግሞ “ስለ እርሻችንና ስለ ወይን ተክላችን መንግሥት የጠየቀንን ግብር ለመክፈል የገንዘብ ብድር ተበድረናል፤


ክፉ ሰው የተበደረውን አይመልስም፤ ደግ ሰው ግን በልግሥና ይሰጣል።


የእንስሳውን ዋጋ ይክፈል፤ ገንዘቡን ለእንስሳው ባለቤት ከከፈለ በኋላ የሞተውን እንስሳ ለራሱ ያስቀር።


ያ ሰው የእግዚአብሔር አገልጋዮች ወደሆኑት ዳኞች ዘንድ ይሂድ፤ የሰውዬውን እንስሳ አለመስረቁንም በመሐላ ያረጋግጥ፤ እንስሳው ያልተሰረቀ ከሆነ የእንስሳው ባለቤት ካሳ አይጠይቅ፤ እንስሳው የጠፋበትም ሰው ካሳ አይክፈል።


እንስሳውን አውሬ በልቶት ከሆነ ሰውየው የአውሬውን ትራፊ ለማስረጃ ያቅርብ፤ አውሬ ስለ ገደለውም እንስሳ ካሳ አይክፈል።


ነገር ግን ይህ የሆነው ባለንብረቱ ባለበት ከሆነ ሰውየው ካሳ መክፈል የለበትም፤ በኪራይ መልክ የወሰደው ከሆነ የተከፈለው ገንዘብ ጒዳቱን ያካክሳል።


የሌላን ሰው እንስሳ የገደለ ምትኩን ይክፈል፤ ይህም ዐይነቱ ሥርዓት በሕይወት ምትክ ሕይወት መሆኑ ነው።


ለሚለምንህ ስጥ፤ ከአንተ መበደር ለሚፈልግ እምቢ አትበለው።”


እናንተ ግን ጠላቶቻችሁን ውደዱ! መልካም ነገርም አድርጉላቸው፤ ‘ብድራችን ይመለስልናል’ ብላችሁ ተስፋ ሳታደርጉ አበድሩ፤ ይህን ብታደርጉ ዋጋችሁ ትልቅ ይሆናል፤ የልዑል እግዚአብሔር ልጆችም ትሆናላችሁ፤ እርሱ ለውለታ ቢሶችና ለክፉዎች እንኳ ሳይቀር ቸር ነው።


አፈጻጸሙም እንደሚከተለው ነው፤ ለእስራኤላዊ ወገኑ ገንዘብ ያበደረ ሁሉ ያበደረውን ብድር ይሰርዝለት፤ እግዚአብሔር የዕዳ መሰረዣ ዓመት ነው ብሎ ያወጀበት ዓመት ስለ ሆነ ከእስራኤላዊ ወገኑ ያበደረውን ገንዘብ ለመቀበል አይፈልግ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos