ዘፀአት 12:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጎቻችሁንም፥ ላሞቻችሁንም ውሰዱ፤ ሂዱም፤ እኔንም ደግሞ ባርኩኝ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዳላችሁት የበግና የፍየል መንጋችሁን፣ የቀንድና የጋማ ከብቶቻችሁን ይዛችሁ ሂዱ፤ እኔንም ባርኩኝ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዳላችሁትም መንጎቻችሁንና ከብቶቻችሁን ውሰዱ፥ ሂዱም፥ እኔንም ደግሞ ባርኩኝ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የበግ፥ የፍየልና የቀንድ ከብት መንጋችሁን ሁሉ ይዛችሁ ሂዱ፤ እኔንም ባርኩኝ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዳላችሁም መንጎቻችሁንና ከብቶቻችሁን ውሰዱ፤ ሂዱም፤ እኔንም ደግሞ ባርኩኝ” አለ። |
ዔሳውም አባቱን ይስሐቅን አለው፥ “አባቴ ሆይ፥ በረከትህ አንዲት ብቻ ናትን? አባቴ ሆይ፥ እኔንም ደግሞ ባርከኝ።” ዔሳውም ጮሆ አለቀሰ።
ከብቶቻችን ከእኛ ጋር ይሄዳሉ፤ አንድ ሰኰናም አይቀርም፤ አምላካችንን እግዚአብሔርን ለማምለክ ከእነርሱ እንወስዳለንና፤ አምላካችንን እግዚአብሔርን እንደምናመልከው ከዚያ እስክንደርስ አናውቅም።”
ሙሴም አለው፥ “እኛ ከታናናሾቻችንና ከሽማግሌዎቻችን፥ ከወንዶችና ሴቶች ልጆቻችን ጋር እንሄዳለን፤ በጎቻችንንና ላሞቻችንንም እንወስዳለን። የአምላካችን የእግዚአብሔር በዓል ነውና።”
ፈርዖንም፥ “ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ በምድረ በዳ ትሠዉ ዘንድ እለቅቃችኋለሁ፤ ነገር ግን በጣም ርቃችሁ አትሂዱ፤ ወደ እግዚአብሔርም ጸልዩልኝ” አለ።
እንግዲህ ወደ እግዚአብሔር ጸልዩልኝ፤ የአምላክ ነጐድጓድ፥ በረዶውም፥ እሳቱም ጸጥ ይላል፤ እኔም እለቅቃችኋለሁ፤ ከዚያም በኋላ ከዚህ አትቀመጡም” አላቸው።