እርሱም፥ “አንተ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል አጥብቀህ ብትሰማ፥ በፊቱም መልካምን ብታደርግ፥ ትእዛዙንም ብታደምጥ፥ ሥርዐቱንም ሁሉ ብትጠብቅ፥ በግብፃውያን ላይ ያመጣሁትን በሽታ አላደርስብህም፤ እኔ ፈዋሽህ እግዚአብሔር ነኝና” አለ።
ዘዳግም 6:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መልካምም ይሆንልህ ዘንድ፥ እግዚአብሔርም ለአባቶችህ ወደ ማለላቸው ወደ መልካሚቱ ምድር ገብተህ እርስዋን ትወርስ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት ቅኑንና መልካሙን አድርግ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መልካም እንዲሆንልህና እግዚአብሔር ለአባቶችህ በመሐላ እንድትወርሳት፣ በእግዚአብሔር ፊት ተስፋ የሰጣቸውን መልካሚቱን ምድር ገብተህ ቀናና መልካም የሆነውን አድርግ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መልካም እንዲሆንልህ፥ ጌታም ለአባቶችህ ወደ ማለላቸው ወደ መልካሚቱ ምድር ገብተህ እርሷን እንድትወርስ በጌታ ፊት ትክክልና መልካሙን አድርግ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእግዚአብሔር ዘንድ ትክክልና መልካም የሆነውን ሁሉ አድርግ፤ ይህን ብታደርግ ሁሉ ነገር በመልካም ሁኔታ ይከናወንልሃል፤ እግዚአብሔር ለቀድሞ አባቶችህ በገባውም ተስፋ ቃል መሠረት መልካሚቱን ምድር ትወርሳለህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መልካምም ይሆንልህ ዘንድ፥ እግዚአብሔርም ለአባቶችህ ወደ ማለላቸው ወደ መልካሚቱ ምድር ገብተህ እርስዋን ትወርስ ዘንድ፥ እግዚአብሔርም እንደ ተናገረ ጠላቶችህን ሁሉ ከፊትህ ያወጣልህ ዘንድ፥ በእግዚአብሔር ፊት ቅኑንና መልካሙን አድርግ። |
እርሱም፥ “አንተ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል አጥብቀህ ብትሰማ፥ በፊቱም መልካምን ብታደርግ፥ ትእዛዙንም ብታደምጥ፥ ሥርዐቱንም ሁሉ ብትጠብቅ፥ በግብፃውያን ላይ ያመጣሁትን በሽታ አላደርስብህም፤ እኔ ፈዋሽህ እግዚአብሔር ነኝና” አለ።
ክፉ ምክርን መክረዋልና ለነፍሳቸው ወዮላት! እንዲህም አሉ፥ “ጻድቁን እንሻረው፤ ሸክም ሆኖብናልና፤” ስለዚህ የእጃቸውን ሥራ ፍሬ ይበላሉ።
“አቤቱ፥ በፊትህ በእውነትና በቅን ልብ እንደ ሄድሁ፥ በፊትህም ደስ የሚያሰኝህን እንዳደረግሁ አስብ።” ሕዝቅያስም እጅግ ታላቅ ልቅሶን አለቀሰ።
“እናንተ ግን፦ ልጅ የአባቱን ኀጢአት ስለ ምን አይሸከምም? ትላላችሁ። ልጅ ፍርድንና ቅን ነገርን በአደረገ፥ ትእዛዜንም ሁሉ በጠበቀና በአደረገ ጊዜ ፈጽሞ በሕይወት ይኖራል።
“ኀጢአተኛውም ከአደረጋት ኀጢአት ሁሉ ቢመለስ፥ ትእዛዜንም ሁሉ ቢጠብቅ፥ ፍርድንና ቅን ነገርንም ቢያደርግ ፈጽሞ በሕይወት ይኖራል እንጂ አይሞትም።
ከእንግዲህ ወዲያ ጣዖት ለኤፍሬም ምንድን ነው? እኔ አደከምሁት፤ አጸናሁትም፤ እኔ እንደ ተወደደ አበባ አፈራዋለሁ፤ ፍሬህም በእኔ ዘንድ ይገኛል።
ይህን ዓለም አትምሰሉ፤ ልባችሁንም አድሱ፤ እግዚአብሔር የሚወደውን መልካሙንና እውነቱን፥ ፍጹሙንም መርምሩ።
በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት መልካምና ጥሩ የሆነውን ነገር ስታደርግ ለአንተ፥ ከአንተም በኋላ ለልጆችህ መልካም እንዲሆንላችሁ፥ አትብላው።
በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት መልካምና ጥሩ የሆነውን ነገር ስታደርግ ለአንተ፥ ከአንተም በኋላ ለልጆችህ ለዘለዓለም መልካም ይሆንላችሁ ዘንድ እኔ የማዝዝህን እነዚህን ቃሎች ሁሉ ሰምተህ ጠብቅ።
ዛሬም እኔ የማዝዝህን ትእዛዝ ሁሉ ብትጠብቅ፥ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት መልካምና ጥሩ የሆነውን ብታደርግ፥ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል ብትሰማ ለእርሱ ልጅ ትሆናለህ።
ለእናንተ፥ ከእናንተም በኋላ ለልጆቻችሁ መልካም ይሆን ዘንድ፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር ለዘለዓለም በሚሰጣችሁ ምድር ዕድሜአችሁ ይረዝም ዘንድ፥ እኔ ዛሬ የማዝዛችሁን ሥርዐቱንና ትእዛዙን ጠብቁ።”
ለእነርሱ፥ ለዘለዓለምም ለልጆቻቸው መልካም ይሆንላቸው ዘንድ፥ እንዲፈሩኝ፥ ሁልጊዜም ትእዛዜን ሁሉ እንዲጠብቁ እንዲህ ያለ ልብ ማን በሰጣቸው፥
በሕይወት እንድትኖሩ፥ መልካምም እንዲሆንላችሁ፥ በምትወርሱአትም ምድር ዕድሜአችሁ እንዲረዝም፥ እግዚአብሔር አምላካችሁ ባዘዛችሁ መንገድ ሁሉ ሂዱ።”
“አምላክህ እግዚአብሔር ለአንተ ሊሰጣት ለአባቶችህ ለአብርሃምና ለይስሐቅ፥ ለያዕቆብም ወደ ማለላቸው ምድር ባገባህ ጊዜ፤ ያልሠራሃቸውንም ታላቅና መልካም ከተሞች፥
“ዛሬ እኔ አንተን የማዝዘውን ትእዛዙንና ፍርዱን፥ ሥርዐቱንም ባለመጠበቅ አምላክህን እግዚአብሔርን እንዳትረሳ ተጠንቀቅ፤