የእስራኤልም ልጆች ከራምሴ ተነሥተው ወደ ሱኮት ሄዱ፤ ከጓዝ ጋር ካሉት ሌላ ስድስት መቶ ሺህ ሰው የሚያህል እግረኛ ነበረ።
ዘዳግም 26:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ፥ በታላቅም ግርማ፥ በታላቅ ተአምራትም፥ በድንቅም ከግብፅ አወጣን፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ የተነሣ እግዚአብሔር በብርቱ እጅና በተዘረጋች ክንድ፣ በታላቅ ድንጋጤ፣ በታምራዊ ምልክትና በድንቅ ከግብጽ አወጣን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም በብርቱ እጅና በተዘረጋች ክንድ፥ በታላቅ ድንጋጤ፥ በተአምራትና በድንቅም ጌታ ከግብጽ አወጣን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም በታላቅ ኀይሉና ሥልጣኑ ታላቅ ፍርሀትን በማሳደር፥ ሥራዎችን ተአምራትንና ድንቅ ሥራዎችን በማሳየት ከግብጽ አወጣን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ፥ በታላቅም ድንጋጤ፥ በተአምራትም፥ በድንቅም ከግብፅ አወጣን፤ |
የእስራኤልም ልጆች ከራምሴ ተነሥተው ወደ ሱኮት ሄዱ፤ ከጓዝ ጋር ካሉት ሌላ ስድስት መቶ ሺህ ሰው የሚያህል እግረኛ ነበረ።
ሙሴም ሕዝቡን አለ፥ “ከባርነት ቤት ከግብፅ የወጣችሁባትን ይህችን ቀን ዐስቡ፤ እግዚአብሔር ከዚህ ቦታ በበረታች እጅ አውጥቶአችኋልና። ስለዚህ የቦካ እንጀራ አትብሉ።
ስለዚህም ፈጥነህ ለእስራኤል ልጆች እንዲህ በላቸው፥ “እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ከግብፃውያንም ተገዥነት አወጣችኋለሁ፤ ከባርነታቸውም አድናችኋለሁ፤ በተዘረጋ ክንድ፤ በታላቅ ፍርድም እታደጋችኋለሁ፤
በምልክትና በድንቅ ነገር፥ በብርቱ እጅና በተዘረጋች ክንድ፥ በታላቅም ግርማ ሕዝብህን እስራኤልን ከግብፅ ምድር አወጣህ።
በግብፅ ምድር በፈርዖንና በሹሞቹ ሁሉ ላይ፥ በምድሪቱም ሁሉ ላይ ምልክትንና ድንቅን ያደርግ ዘንድ እግዚአብሔር እንደ ላከው ያለ፥
በእስራኤል ሁሉ ፊት በታላቅ ተአምር ሁሉና በጸናች እጅ፥ በተዘረጋችም ክንድ ሁሉ እንዳደረገው እንደ ሙሴ ያለ ነቢይ አልተነሣም።
አምላካችን እግዚአብሔር በዐይናችሁ ፊት በግብፅ ለእናንተ እንደ ሠራው ሁሉ ፥ በፈተናና በተአምራት፥ በድንቅና በሰልፍ፥ በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ፥ በታላቅም ማስፈራራት እግዚአብሔር ከሌላ ሕዝብ መካከል ገብቶ ለእርሱ ሕዝብን ይወስድ ዘንድ ሞክሮ እንደ ሆነ፥
አንተም በግብፅ ባሪያ እንደ ነበርህ አስብ፤ እግዚአብሔር አምላክህ በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ ከዚያ አወጣህ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ ዕለተ ሰንበትን ትጠብቃትና ትቀድሳት ዘንድ አዘዘህ።