በዚያ ጊዜም ሸምበቆ በውኃ ውስጥ እንደሚንቀሳቀስ እግዚአብሔር እንዲሁ እስራኤልን ይመታል፤ እግዚአብሔርንም ያስቈጡ ዘንድ የማምለኪያ አፀድ ተክለዋልና ለአባቶቻቸው ከሰጣቸው ከዚች ከመልካሚቱ ምድር እስራኤልን ይነቅላል፤ በወንዙም ማዶ ይበትናቸዋል።
ዘዳግም 16:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ለአንተ በምትሠራው በአምላክህ በእግዚአብሔር መሠዊያ አጠገብ ከማናቸውም ዛፍ የማምለኪያ ዐጸድ አድርገህ አትትከል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለአምላክህ ለእግዚአብሔር በምትሠራው መሠዊያ አጠገብ የአሼራን ምስል የዕንጨት ዐምድ አታቁም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ለአንተ በምትሠራው በአምላክህ በጌታ መሠዊያ አጠገብ ከማናቸውም ዛፍ የማምለኪያ ዐፀድ አድርገህ አትትከል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ለአምላክህ ለእግዚአብሔር መሠዊያ በምትሠራበት አጠገብ የማምለኪያ ዐፀድ (ዛፍ) አትትከል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለአንተ በምትሠራው በአምላክህ በእግዚአብሔር መሠዊያ አጠገብ ከማናቸውም ዛፍ የማምለኪያ ዐፀድ አድርገህ አትትከል። |
በዚያ ጊዜም ሸምበቆ በውኃ ውስጥ እንደሚንቀሳቀስ እግዚአብሔር እንዲሁ እስራኤልን ይመታል፤ እግዚአብሔርንም ያስቈጡ ዘንድ የማምለኪያ አፀድ ተክለዋልና ለአባቶቻቸው ከሰጣቸው ከዚች ከመልካሚቱ ምድር እስራኤልን ይነቅላል፤ በወንዙም ማዶ ይበትናቸዋል።
አክዓብም የማምለኪያ ዐፀድን አሠራ፤ አክዓብም ሰውነቱ እንድትጠፋ ከእርሱ በፊት ከነበሩት ከእስራኤል ነገሥታት ሁሉ ይልቅ የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን የሚያስቈጣውን ነገር አበዛ።
የአምላካቸውንም የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ሁሉ ተዉ፤ ቀልጠው የተሠሩትንም የሁለቱን እንቦሶች ምስሎች አደረጉ፤ የማምለኪያ ዐፀድንም ተከሉ፤ ለሰማይም ሠራዊት ሁሉ ሰገዱ፤ በዓልንም አመለኩ።
አባቱም ሕዝቅያስ ያፈረሳቸውን የኮረብታውን መስገጃዎች መልሶ ሠራ፤ የእስራኤልም ንጉሥ አክዓብ እንዳደረገው ለበዓል መሠዊያን ሠራ፤ የማምለኪያ ዐፀድንም ተከለ፤ ለሰማይም ሠራዊት ሁሉ ሰገደ አመለካቸውም።
እግዚአብሔርም ለዳዊትና ለልጁ ለሰሎሞን፥ “በዚህ ቤት ከእስራኤልም ነገድ ሁሉ በመረጥኋት በኢየሩሳሌም ስሜን ለዘለዓለም አኖራለሁ፤
አባቱም ሕዝቅያስ ያፈረሳቸውን የኮረብታ መስገጃዎች መልሶ ሠራ፤ ለበዓሊምም መሠዊያ ሠራ፤ የማምለኪያ ዐፀዶችንም ተከለ፤ ለሰማይም ሠራዊት ሁሉ ሰገደ፤ አመለካቸውም።
ነገር ግን መሠውያዎቻቸውን ታፈርሳላችሁ፤ ሐውልቶቻቸውንም ትሰብራላችሁ፤ የማምለኪያ ዐፀዶቻቸውን ትቈርጣላችሁ፤ ጣዖቶቻቸውንም በእሳት ታቃጥላላችሁ፤
“ለእናንተ በእጅ የተሠራ ጣዖት አታድርጉ፤ የተቀረጸም ምስል ወይም ሐውልት አታቁሙ፤ ትሰግዱለትም ዘንድ በምድራችሁ ላይ የተቀረጸ ድንጋይ አታኑሩ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና።
ነገር ግን እንዲህ አድርጉባቸው፤ መሠዊያቸውን አፍርሱ፤ ሐውልቶቻቸውንም ሰባብሩ፥ የማምለኪያ ዐፀዶቻቸውንም ቍረጡ፥ የአማልክቶቻቸውንም ምስል በእሳት አቃጥሉ።
የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አደረጉ፤ አምላካቸውንም እግዚአብሔርን ረስተው በዓሊምንና አስታሮትን አመለኩ።