ዘዳግም 12:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደሙን ግን እንደ ውኃ በምድር ላይ አፍስሱት እንጂ አትብሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደሙን ግን እንደ ውሃ መሬት ላይ አፍስሰው እንጂ አትብላው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደሙን ግን እንደ ውሃ መሬት ላይ አፍስሰው እንጂ አትብላው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ደማቸውን አትብላ፤ ደሙን እንደ ውሃ በመሬት ላይ አፍስሰው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደሙን ግን እንደ ውኃ በምድር ላይ አፍስሰው እንጂ አትብላው። |
ደምዋም በመካከልዋ አለ። በተራቈተ ድንጋይ ላይ አደረገችው እንጂ በአፈር ይከደን ዘንድ በመሬት ላይ አላፈሰሰችውም።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከደም ጋር ትበላላችሁ፤ ዐይናችሁንም ወደ ጣዖቶቻችሁ ታነሣላችሁ፤ ደምንም ታፈስሳላችሁ፤ በውኑ ምድሪቱን ትወርሳላችሁን?
ነገር ግን ለጣዖት ከሚሠዋው፥ ከዝሙት፥ ሞቶ የተገኘውንና ደም ከመብላት እንዲርቁ፥ ለራሳቸው የሚጠሉትንም በወንድሞቻቸው ላይ እንዳያደርጉ እዘዙአቸው።
ለአማልክት የተሠዋውን፥ ሞቶ የተገኘውን፥ ደምንም አትብሉ፤ ከዝሙትም ራቁ፤ በራሳችሁ የምትጠሉትንም በወንድሞቻችሁ ላይ አታድርጉ፥ ከእነዚህ ሥራዎችም ሰውነታችሁን ብትጠብቁ በሰላም ትኖራላችሁ፤ ደኅና ሁኑ።”
ሕዝቡም ወደ ምርኮ ሄዱ፤ በጎችን፥ በሬዎችንም፥ ጥጆችንም ወስደው እንዳገኙ በምድር ላይ አረዱ፤ ሕዝቡም ከደሙ ጋር በሉ።
ለሳኦልም፥ “እነሆ፥ ሕዝቡ ከደሙ ጋር በመብላታቸው እግዚአብሔርን በደሉ” ብለው ነገሩት። ሳኦልም በጌቴም “ትልቅ ድንጋይ አንከባልላችሁ አቅርቡልኝ” አላቸው።