ዘዳግም 11:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አምላክህን እግዚአብሔርን ውደድ፤ ሕጉንም፥ ሥርዐቱንም፥ ትእዛዙንም፥ ፍርዱንም በዘመንህ ሁሉ ጠብቅ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ አምላክህን እግዚአብሔርን ውደድ፤ ግዴታውን፣ ሥርዐቱን፣ ሕጉንና ትእዛዙን ሁልጊዜ ጠብቅ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እንግዲህ ጌታ አምላክህን ውደድ፤ ግዴታውን፥ ሥርዓቱን፥ ሕጉንና ትእዛዙን ሁልጊዜ ጠብቅ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እንግዲህ እግዚአብሔር አምላክህን ውደድ፤ እርሱ ከአንተ የሚፈልገውን ሥርዓቱን፥ ደንቡንና ትእዛዞቹን ሁልጊዜ ፈጽም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ አምላክህን እግዚአብሔርን ውደድ፥ ሕጉንም ሥርዓቱንም ፍርዱንም ትእዛዙንም ሁልጊዜ ጠብቅ። |
ስለዚህ ከእናንተ በፊት የነበሩ ሰዎች የሠሩትን ጸያፍ የሆነውን ወግ ሁሉ እንዳትሠሩ፥ በእርሱም እንዳትረክሱ ሥርዐቴን ጠብቁ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና።”
ቢያረክሱአት እንዳይሞቱ፥ ስለ እርስዋም ኀጢአትን እንዳይሸከሙ፥ ሕግን ይጠብቁ፤ የምቀድሳቸው እኔ እግዚአብሔር ነኝና።
እግዚአብሔር እንዲሁ አዝዞኛልና እንዳትሞቱ በምስክሩ ድንኳን ደጃፍ ሌሊቱንና ቀኑን ሰባት ቀን ተቀመጡ፤ የእግዚአብሔርንም ሥርዐት ጠብቁ፤”
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመንገዴ ብትሄድ ትእዛዜንም ብትጠብቅ፥ በቤቴ ላይ ትፈርዳለህ፥ አደባባዮቼንም ትጠብቃለህ፥ በዚህም ከቆሙት ከእነዚህ ጋር መግባትን እሰጣለሁ።
“እስራኤል ሆይ፥ አሁንስ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ የሚፈልገው ምንድን ነው? አምላክህን እግዚአብሔርን ትፈራ ዘንድ፥ በመንገዱም ሁሉ ትሄድ ዘንድ፥ አምላክህንም እግዚአብሔርን ትወድድ ዘንድ፥ በፍጹምም ልብህ፥ በፍጹምም ነፍስህ ታመልከው ዘንድ ነው እንጂ፥
“እናንተ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ትወድዱ ዘንድ፥ በፍጹም ልባችሁ፥ በፍጹምም ነፍሳችሁ ታመልኩት ዘንድ ዛሬ ለእናንተ የማዝዘውን ትእዛዜን ፈጽማችሁ ብትሰሙ፥
አምላካችሁን እግዚአብሔርን ትወድዱ ዘንድ፥ በመንገዱም ሁሉ ትሄዱ ዘንድ፥ እርሱንም ትከተሉ ዘንድ፥ ዛሬ ለእናንተ የማዝዘውን ትእዛዝ ሁሉ ብትጠብቁ ብታደርጉአትም፥
በሕይወትም እንድትኖር፥ አምላክህን እግዚአብሔርንም በፍጹም ልብህ፥ በፍጹምም ነፍስህ እንድትወድድ እግዚአብሔር ልብህን፥ የዘርህንም ልብ ያጠራዋል።
“አሁንም እስራኤል ሆይ፥ እንድታደርጉአቸው፥ በሕይወትም እንድትኖሩ፥ እንድትበዙም፥ የአባቶቻችሁም አምላክ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ምድር ገብታችሁ እንድትወርሱ፥ ዛሬ የማስተምራችሁን ሥርዐትና ፍርድ ስሙ።
ለእናንተ፥ ከእናንተም በኋላ ለልጆቻችሁ መልካም ይሆን ዘንድ፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር ለዘለዓለም በሚሰጣችሁ ምድር ዕድሜአችሁ ይረዝም ዘንድ፥ እኔ ዛሬ የማዝዛችሁን ሥርዐቱንና ትእዛዙን ጠብቁ።”
እነሆ፥ እናንተ ገብታችሁ በምትወርሱአት ምድር ውስጥ እንዲህ ታደርጉ ዘንድ አምላኬ እግዚአብሔር እንዳዘዘኝ ሥርዐትና ፍርድን አሳየኋችሁ።
ሙሴም እስራኤልን ሁሉ ጠርቶ አላቸው፥ “እስራኤል ሆይ እንድትማሩአትም፥ በማድረግም እንድትጠብቁአት ዛሬ በጆሮአችሁ የምናገራትን ሥርዐትና ፍርድ ስሙ።
ለእነርሱ፥ ለዘለዓለምም ለልጆቻቸው መልካም ይሆንላቸው ዘንድ፥ እንዲፈሩኝ፥ ሁልጊዜም ትእዛዜን ሁሉ እንዲጠብቁ እንዲህ ያለ ልብ ማን በሰጣቸው፥
“ልትወርሱአት በምትገቡባት ምድር ታደርጉት ዘንድ አምላካችሁ እግዚአብሔር እንዳስተምራችሁ ያዘዘው ትእዛዝና ሥርዐት፥ ፍርድም ይህ ነው።