ሐዋርያት ሥራ 21:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያ ጊዜም ጭፍሮቹን ከአለቆቻቸው ጋር ይዞ ወደ እነርሱ ሄደ፤ እነርሱም የሻለቃውን ጭፍሮች ባዩ ጊዜ ጳውሎስን መምታታቸውን ተዉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም ወዲያው አንዳንድ የጦር መኰንኖችንና ወታደሮችን ይዞ እየሮጠ ወደ እነርሱ ወረደ፤ እነርሱም መኰንኖቹንና ወታደሮቹን ባዩ ጊዜ ጳውሎስን መደብደብ ተዉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ያንጊዜ ወታደሮችን ከመቶ አለቆች ጋር ይዞ እየሮጠ ወደ እነርሱ ወረደ፤ እነርሱም የሻለቃውንና ወታደሮችን ባዩ ጊዜ ጳውሎስን መምታት ተዉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ እርሱ ወታደሮችንና የመቶ አለቆችን አስከትሎ በፍጥነት እየሮጠ ወደ ሰዎቹ ሄደ። ሰዎቹም አዛዡንና ወታደሮቹን ባዩ ጊዜ ጳውሎስን መደብደብ ተዉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም ያን ጊዜ ወታደሮችን ከመቶ አለቆች ጋር ይዞ እየሮጠ ወረደባቸው፤ እነርሱም የሻለቃውንና ወታደሮችን ባዩ ጊዜ ጳውሎስን መምታት ተዉ። |
አረማውያንም ሁሉ የምኵራቡን አለቃ ሶስቴንስን ይዘው በሸንጎ ፊት ደበደቡት፤ የእርሱም ነገር ጋልዮስን ምንም አላሳዘነውም።
እኔም እንዲህ አልሁት፦ ‘ጌታዬ ሆይ፥ በአንተ የሚያምኑትን በየምኵራቦቻቸው ሳስራቸውና ስደበድባቸው የነበርሁ እኔ እንደ ሆንሁ እነርሱ ያውቃሉ።
ይህን ሰው አይሁድ ያዙት፤ ሊገድሉትም ፈለጉ፤ ከወታደሮችም ጋር ተከላከልሁለት፥ የሮም ሰው መሆኑንም ዐውቄ አዳንሁት።
እሺም አሰኛቸው፤ ሐዋርያትንም ጠርተው ገረፉአቸው፤ እንግዲህ ወዲህም በኢየሱስ ስም እንዳያስተምሩ ገሥጸው ተዉአቸው።