Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 21:32 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 ስለዚህ እርሱ ወታደሮችንና የመቶ አለቆችን አስከትሎ በፍጥነት እየሮጠ ወደ ሰዎቹ ሄደ። ሰዎቹም አዛዡንና ወታደሮቹን ባዩ ጊዜ ጳውሎስን መደብደብ ተዉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 እርሱም ወዲያው አንዳንድ የጦር መኰንኖችንና ወታደሮችን ይዞ እየሮጠ ወደ እነርሱ ወረደ፤ እነርሱም መኰንኖቹንና ወታደሮቹን ባዩ ጊዜ ጳውሎስን መደብደብ ተዉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 እርሱም ያንጊዜ ወታደሮችን ከመቶ አለቆች ጋር ይዞ እየሮጠ ወደ እነርሱ ወረደ፤ እነርሱም የሻለቃውንና ወታደሮችን ባዩ ጊዜ ጳውሎስን መምታት ተዉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 በዚያ ጊዜም ጭፍ​ሮ​ቹን ከአ​ለ​ቆ​ቻ​ቸው ጋር ይዞ ወደ እነ​ርሱ ሄደ፤ እነ​ር​ሱም የሻ​ለ​ቃ​ውን ጭፍ​ሮች ባዩ ጊዜ ጳው​ሎ​ስን መም​ታ​ታ​ቸ​ውን ተዉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 እርሱም ያን ጊዜ ወታደሮችን ከመቶ አለቆች ጋር ይዞ እየሮጠ ወረደባቸው፤ እነርሱም የሻለቃውንና ወታደሮችን ባዩ ጊዜ ጳውሎስን መምታት ተዉ።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 21:32
8 Referencias Cruzadas  

የሕዝቤን ቅስም ልትሰብሩና ድኾችንም ልትበዘብዙ መብት የላችሁም፤ ይህን የተናገርኩ እኔ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ነኝ።”


ከዚህ በኋላ ወታደሮቹና አዛዣቸው፥ የአይሁድ የዘብ ኀላፊዎችም ኢየሱስን ይዘው አሰሩት።


በዚህ ጊዜ ሁሉም የምኲራብ አለቃውን ሶስቴንስን ይዘው በሸንጎው ፊት ደበደቡት፤ ይህ ሁሉ ሲሆን ጋልዮስ ደንታ አልነበረውም።


እኔም እንዲህ አልኩ፤ ‘ጌታ ሆይ! በየምኲራቡ እየሄድኩ በአንተ ያመኑትን ሁሉ እንዳሰርኩና እንደ ደበደብኩ እነርሱ ራሳቸው ያውቃሉ።


ይህን ሰው አይሁድ ይዘው ሊገድሉት ነበር፤ እኔ ግን የሮም ዜጋ መሆኑን ስላወቅሁ ከወታደሮች ጋር ደርሼ አዳንኩት።


ቤተ መቅደስንም ሊያረክስ ሲሞክር ይዘነዋል፤ [በሕጋችንም መሠረት ልንፈርድበት አስበን ነበር፤


ከዚህ በኋላ ሐዋርያቱን ወደ እነርሱ ጠርተው አስገረፉአቸው፤ የኢየሱስንም ስም በመጥራት እንዳይናገሩ አዘዙአቸውና ለቀቁአቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos