ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያሳየውና ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና።”
2 ነገሥት 8:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤልሳዕም፥ “ሂድ፥ መዳንስ ትድናለህ በለው፤ ነገር ግን እንዲሞት እግዚአብሔር አሳይቶኛል” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤልሳዕም፣ “ሂድና፣ ‘መዳኑንስ በርግጥ ትድናለህ’ በለው፤ ነገር ግን እንደሚሞት እግዚአብሔር ገልጾልኛል” ሲል መለሰለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤልሳዕም “ቤንሀዳድ እንደሚሞት እግዚአብሔር ገልጦልኛል፤ አንተ ግን ትድናለህ ብለህ ንገረው” አለው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኤልሳዕም “ቤንሀዳድ እንደሚሞት እግዚአብሔር ገልጦልኛል፤ አንተ ግን ትድናለህ ብለህ ንገረው” አለው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤልሳዕም “ሂድ፤ ‘መዳንስ ትድናለህ፤’ በለው፤ ነገር ግን እንዲሞት እግዚአብሔር አሳይቶኛል፤” አለው። |
ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያሳየውና ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና።”
ወደ ንጉሡም ደረሰ። ንጉሡም፥ “ሚክያስ ሆይ! ወደ ሬማት ዘገለዓድ ለሰልፍ እንሂድን? ወይስ እንቅር?” አለው። እርሱም፥ “ውጣና ተከናወን፤ እግዚአብሔርም በንጉሡ እጅ አሳልፎ ይሰጣታል” ብሎ መለሰለት።
ኤልያስም፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የአቃሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን ትጠይቅ ዘንድ መልእክተኞችን ለምን ላክህ? በእስራኤል ዘንድ አምላክ ስለሌለ ነውን? እንደዚህ አይደለም፤ ትሞታለህ እንጂ ከወጣህበት አልጋ አትወርድም” አለው።
ነገሩ እንዲህ አይደለም፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ትሞታለህ እንጂ ከወጣህበት አልጋ አትወርድም በላቸው” አለው። ኤልያስም ሄደ፤ እንዲሁም ነገራቸው።
በአራጣ ቢያበድር፥ አትርፎም ቢወስድ፥ እንደዚህ ያለ ሰው በሕይወት አይኖርም፤ ይህን ርኵሰት ሁሉ አድርጎአልና ፈጽሞ ይሞታል፤ ደሙም በላዩ ይሆናል።
ጌታ እግዚአብሔርም እንዲህ አሳየኝ፤ እነሆም ጌታ እግዚአብሔር ለመፍረድ በቃሉ እሳትን ጠራ፤ እርስዋም ታላቁን ቀላይና ምድርን በላች።