1 ሳሙኤል 13:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ፦ ፍልስጥኤማውያን አሁን ወደ እኔ ወደ ጌልጌላ ይወርዱብኛል፤ እኔም የእግዚአብሔርን ፊት አልለመንሁም አልሁ፤ ስለዚህም ደፍሬ የሚቃጠል መሥዋዕትን አሳረግሁ” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ‘ስለዚህ ፍልስጥኤማውያን ወርደው ወደ ጌልገላ ይመጡብኛል፤ እኔም የእግዚአብሔርን ሞገስ አልለመንሁም’ ብዬ አሰብሁ። ስለዚህ የሚቃጠል መሥዋዕት ማቅረብ ግድ ሆነብኝ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ፍልስጥኤማውያን ወርደው ወደ ጌልገላ ይመጡብኛል፤ እኔም የጌታን ርዳታ አልለመንሁም፥ ብዬ አሰብሁ። ስለዚህ የሚቃጠል መሥዋዕት ማቅረብ ግድ ሆነብኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም ‘ፍልስጥኤማውያን ገና በጌልገላ ሳለሁ አደጋ ሊጥሉብኝ ነው የእግዚአብሔርንም ርዳታ ገና አለመንኩም’ ብዬ አሰብኩ፤ መሥዋዕት ማቅረብ እንደሚገባኝም ተረዳሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰለዚህ፦ ፍልስጥኤማውያን አሁን ወደ ጌልገላ ይወርዱብኛል፥ እኔም የእግዚአብሔርን ሞገስ አልለመንሁም አልሁ፥ ስለዚህም ሳልታገሥ የሚቃጠልን መሥዋዕት አሳረግሁ አለ። |
“እህልን እንሸጥ ዘንድ መባቻው መቼ ያልፋል? የኢፍ መስፈሪያውንም እያሳነስን፥ ሰቅሉንም እያበዛን፥ በሐሰተኛም ሚዛን እያታለልን፥
ሳሙኤልም፥ “ያደረግኸው ምንድን ነው?” አለ። ሳኦልም፥ “ሕዝቡ ከእኔ ተለይተው እንደ ተበታተኑ፥ አንተም በነገርኸኝ መሠረት በቀጠሮው ቀን እንዳልመጣህ፥ ፍልስጥኤማውያንም ወደ ማኪማስ እንደ ተሰበሰቡ አየሁ፤
ሳሙኤልም ሳኦልን፥ “በድለኻል፤ አምላክህ እግዚአብሔር ያዘዘህን ትእዛዙን አልጠበቅህምና፤ ዛሬ እግዚአብሔር መንግሥትህን በእስራኤል ላይ ለዘለዓለም አጽንቶልህ ነበር።
ሳሙኤልም እስራኤልን ለመገናኘት በጥዋት ገሥግሦ ሄደ። ለሳሙኤልም፥ “ሳኦል ወደ ቀርሜሎስ መጣ፤ እነሆም፥ ለራሱ የመታሰቢያ ዐምድ አቆመ” ብለው ነገሩት። ሳሙኤልም ሰረገላውን መልሶ ወደ ጌልጌላ ወደ ሳኦል ወረደ፤ ከአማሌቅ ዘንድ ከአመጣውም ከአማረው ከምርኮው መንጋ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ሲሠዋ አገኘው፤
ሳሙኤልም ሳኦልን፥ “በውኑ የእግዚአብሔርን ቃል በመስማት ደስ እንደሚለው እግዚአብሔር በሚቃጠልና በሚታረድ መሥዋዕት ደስ ይለዋልን? እነሆ፥ መታዘዝ ከመሥዋዕት፥ ማዳመጥም የአውራ በግ ስብ ከማቅረብ ይበልጣል።
በዚያም ቀን ከሳኦል አገልጋዮች አንድ ሰው በኔሴራ አቅራቢያ በዚያ በእግዚአብሔር ፊት ነበር፤ ስሙም ሶርያዊው ዶይቅ ነበረ፤ የሳኦልም በቅሎዎች ጠባቂ ነበረ።