Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ሳሙኤል 13:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ስለዚህ ፍልስጥኤማውያን ወርደው ወደ ጌልገላ ይመጡብኛል፤ እኔም የጌታን ርዳታ አልለመንሁም፥ ብዬ አሰብሁ። ስለዚህ የሚቃጠል መሥዋዕት ማቅረብ ግድ ሆነብኝ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ‘ስለዚህ ፍልስጥኤማውያን ወርደው ወደ ጌልገላ ይመጡብኛል፤ እኔም የእግዚአብሔርን ሞገስ አልለመንሁም’ ብዬ አሰብሁ። ስለዚህ የሚቃጠል መሥዋዕት ማቅረብ ግድ ሆነብኝ።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ስለዚህም ‘ፍልስጥኤማውያን ገና በጌልገላ ሳለሁ አደጋ ሊጥሉብኝ ነው የእግዚአብሔርንም ርዳታ ገና አለመንኩም’ ብዬ አሰብኩ፤ መሥዋዕት ማቅረብ እንደሚገባኝም ተረዳሁ።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ስለ​ዚህ፦ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን አሁን ወደ እኔ ወደ ጌል​ጌላ ይወ​ር​ዱ​ብ​ኛል፤ እኔም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፊት አል​ለ​መ​ን​ሁም አልሁ፤ ስለ​ዚ​ህም ደፍሬ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትን አሳ​ረ​ግሁ” አለ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ሰለዚህ፦ ፍልስጥኤማውያን አሁን ወደ ጌልገላ ይወርዱብኛል፥ እኔም የእግዚአብሔርን ሞገስ አልለመንሁም አልሁ፥ ስለዚህም ሳልታገሥ የሚቃጠልን መሥዋዕት አሳረግሁ አለ።

Ver Capítulo Copiar




1 ሳሙኤል 13:12
9 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔርን እንዲህ በሉት፦ “ሥራህ እንዴት ግሩም ነው፥ ኃይልህ ብዙ ሲሆን ጠላቶች ዋሹብህ።


እናንተ እንዲህ ትላላችሁ፦ “እህልን እንድንሸጥ መባቻው መቼ ያልፋል? ስንዴውንም ለሽያጭ ገበያ ለማቅረብ ሰንበት መቼ ያበቃል? የኢፍ መስፈሪያውንም እናሳንሳለን፥ ሰቅሉንም እናበዛለን፥ በሐሰተኛም ሚዛን እናታልላለን፥


እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና፥ እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበው ይስጥ፤ በኀዘን ወይም በግድ ግን አይሁን።


ሳሙኤል ግን “ያደረግኸው ነገር ምንድነው?” ሲል ጠየቀው። ሳኦልም እንዲህ ሲል መለሰ፤ ሠራዊቱ መበታተኑን፥ አንተም በቀጠርኸው ጊዜ አለመምጣትህን፥ ፍልስጥኤማውያንም በማክማስ መሰብሰባቸውን አየሁ፤


ሳሙኤልም እንዲህ አለ፤ “የማይገባህን አደረግህ፤ አምላክህ ጌታ የሰጠህን ትእዛዝ አልጠበቅህም፤ ዛሬ መንግሥትህን በእስራኤል ላይ ለዘለዓለም ባጸናልህ ነበር፤


ሳሙኤልም ጠዋት ተነሥቶ በማለዳ ሳኦልን ለመገናኘት ሄደ፤ ነገር ግን፥ “ሳኦል ወደ ቀርሜሎስ ሄዷል፤ ለራሱ ክብር የመታሰቢያ ሐውልት በዚያ ካቆመ በኋላ ተመልሶ ወደ ጌልገላ ወርዷል” ተብሎ ተነገረው።


ሳሙኤልም፦ “ጌታ ለቃሉ በመታዘዝ ደስ የሚለውን ያህል፥ ጌታ፥ በሚቃጠል ቁርባንና መሥዋዕት ደስ ይለዋልን? እነሆ! መታዘዝ ከመሥዋዕት፥ ማዳመጥም ከአውራ በግ ሥብ ይበልጣል።


በዚያችም ዕለት ከሳኦል አገልጋዮች አንዱና የእረኞቹ አለቃ የሆነው ኤዶማዊው ዶይቅ እዚያው በጌታ ፊት እንዲቆይ ተገዶ ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos