የሰሎሞንንም የማዕዱን መብል፥ የብላቴኖቹንም አቀማመጥ፥ የሎሌዎቹንም ሥርዐት፥ አለባበሳቸውንም፥ ጠጅ አሳላፊዎቹንም፥ በእግዚአብሔርም ቤት የሚያቀርበውን መሥዋዕት ባየች ጊዜ ተደነቀች።
1 ዜና መዋዕል 26:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሶፊምና ለሖሳም በምዕራብ በኩል በዐቀበቱ መንገድ ባለው በሸለኬት በር በኩል ጥበቃ በጥበቃ ላይ ዕጣ ወጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምዕራቡ በርና በላይኛው መንገድ ላይ የሚገኘው የሸሌኬት በር ዕጣዎች ለሰፊንና ለሖሳ ወጣ። በአንዱ ዘብ ጥበቃ ትይዩ ሌላ ዘብ ጥበቃ ነበረ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለሰፊንና ለሖሳ በዐቀበቱም መንገድ ባለው በሸሌኬት በር በምዕራብ በኩል ዕጣ ወጣላቸው፤ ይህም ጥበቃ ከጥበቃ ትይዩ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለሹፒምና ለሖሳ በምዕራብ በኩል የሚገኘው ቅጽር በርና በላይኛው መንገድ በኩል የሚገኘው ሻሌኬት ተብሎ የሚጠራው ቅጽር በር ደረሳቸው፤ የዘብ ጥበቃው አገልግሎት በክፍለ ጊዜ የተመደበ ሆኖ ቅደም ተከተል ተራ የያዘ ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለሰፊንና ለሖሳ በምዕራብ በኩል፥ በዐቀበቱም መንገድ ባለው በሸሌኬት በር በኩል በጥበቃ ላይ ጥበቃ ዕጣ ወጣባቸው። |
የሰሎሞንንም የማዕዱን መብል፥ የብላቴኖቹንም አቀማመጥ፥ የሎሌዎቹንም ሥርዐት፥ አለባበሳቸውንም፥ ጠጅ አሳላፊዎቹንም፥ በእግዚአብሔርም ቤት የሚያቀርበውን መሥዋዕት ባየች ጊዜ ተደነቀች።
በምሥራቅ በኩል ለየዕለቱ ስድስት፥ በሰሜን በኩል ለየዕለቱ አራት፥ በደቡብ በኩል ለየዕለቱ አራት፥ ለዕቃ ቤትም ሁለት ሁለት ነበሩ።
በኦሳም በምዕራብ በኩል በሸለኬት በር ሦስት፥ በምሥራቅ በኩል በዐቀበቱ በር ከጥበቃ በላይ ጥበቃ በቀን ስድስት፥ በሰሜን በኩል አራት፥ በደቡብ በኩል አራት፥ በዕቃ ቤቱ በኩል ተቀባባዮች ሁለት ሁለት፥ በምዕራብ በኩል አራት በመተላለፊያውም መንገድ ተቀባባዮች ሁለት ሁለት።
የማዕዱንም መብል፥ የብላቴኖቹንም አቀማመጥ፥ የሎሌዎቹንም ሥርዐት፥ አለባበሳቸውንም፥ ጠጅ አሳላፊዎቹንም፥ አለባበሳቸውንም፥ በእግዚአብሔርም ቤት የሚያሳርገውን መሥዋዕት ባየች ጊዜ ተደነቀች።
የሌዋውያኑም አለቆች አሳብያ፥ ሰርብያ፥ ኢያሱ፥ የቀድምኤልም ልጆች፥ ወንድሞቻቸውም እንደ እግዚአብሔር ሰው እንደ ዳዊት ትእዛዝ በየሰሞናቸው በእነርሱ ፊት ያከብሩና ያመሰግኑ ነበር።