Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 25:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ሁሉም ተካ​ክ​ለው፥ ታና​ሹም ታላ​ቁም፥ ለሰ​ሞ​ና​ቸው ዕጣ ተጣ​ጣሉ እነ​ር​ሱም ፍጹ​ማ​ንና የተ​ማሩ ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 የሥራ ድርሻቸውንም ለመወሰን ወጣት፣ ሽማግሌ፣ መምህርም ሆነ ደቀ መዝሙር ሳይባል እኩል ዕጣ ተጣጣሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ታናሹ እንደ ታላቁ፥ አስተማሪው እንደ ተማሪው፥ ሁሉም በተመሳሳይ መልኩ፥ ለሰሞናቸው ዕጣ ተጣጣሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 የሥራ ምድባቸውን ለመወሰን ወጣት ሆነ ሽማግሌ፥ አስተማሪም ሆነ ተማሪ ለማንም ልዩነት ሳይደረግ ዕጣ ይጣጣሉ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ሁሉም ተካክለው፥ ታናሹ እንደ ታላቁ፥ አስተማሪው እንደ ተማሪው፥ ለሰሞናቸው ዕጣ ተጣጣሉ።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 25:8
13 Referencias Cruzadas  

የሌ​ዋ​ው​ያ​ኑም አለቃ ኮነ​ን​ያስ በዜማ ላይ ተሾሞ ነበር። ብል​ሃ​ተኛ ነበ​ረና።


እነ​ዚ​ህም ደግሞ በን​ጉሡ በዳ​ዊ​ትና በሳ​ዶቅ በአ​ቤ​ሜ​ሌ​ክም በሌ​ዋ​ው​ያ​ንና በካ​ህ​ናት አባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች ፊት፥ ታላ​ላ​ቆች እንደ ታና​ናሽ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው፥ እንደ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው እንደ አሮን ልጆች ዕጣ ተጣ​ጣሉ።


ከአ​ል​ዓ​ዛ​ርና ከኢ​ታ​ም​ርም ልጆች መካ​ከል የን​ዋ​ያተ ቅዱ​ሳ​ቱና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አለ​ቆች ነበ​ሩና እነ​ዚ​ህና እነ​ዚያ እን​ዲህ በዕጣ ተመ​ደቡ።


ከአ​ሳፍ ልጆች፤ ዘኩር፥ ዮሴፍ፥ ናታ​ንያ፥ ኤራ​ኤል፤ እነ​ዚህ የአ​ሳፍ ልጆች የን​ጉሡ ቀራ​ቢ​ዎች ነበሩ።


የመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ዕጣ ለአ​ሳፍ ወገን ለዮ​ሴፍ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቹና ለል​ጆቹ ለዐ​ሥራ ሁለቱ ደረ​ሳ​ቸው፤ ሁለ​ተ​ኛ​ውም ዕጣ ለጎ​ዶ​ል​ያስ ለል​ጆ​ቹና ለወ​ን​ድ​ሞቹ ለዐ​ሥራ ሁለቱ ደረ​ሳ​ቸው፤


በበ​ሩም ሁሉ ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች ታና​ሹና ታላቁ ተካ​ክ​ለው ዕጣ ተጣ​ጣሉ።


ለሶ​ፊ​ምና ለሖ​ሳም በም​ዕ​ራብ በኩል በዐ​ቀ​በቱ መን​ገድ ባለው በሸ​ለ​ኬት በር በኩል ጥበቃ በጥ​በቃ ላይ ዕጣ ወጣ።


እነ​ሆም፥ ንጉሡ በመ​ግ​ቢ​ያው በዓ​ምዱ አጠ​ገብ ሆኖ በን​ጉ​ሡም ዙሪያ አለ​ቆ​ችና መለ​ከ​ተ​ኞች፥ መኳ​ን​ን​ትም ቆመው አየች። ሕዝ​ቡም ሁሉ ደስ ብሎ​አ​ቸው መለ​ከ​ቱን ይነፉ ነበር፤ መዘ​ም​ራ​ንም በዜማ ዕቃ እያ​ዜሙ የም​ስ​ጋና መዝ​ሙር ይዘ​ምሩ ነበር። ጎቶ​ል​ያም ልብ​ስ​ዋን ቀድዳ፥ “ዐመፅ ነው! ዐመፅ ነው!” ብላ ጮኸች።


የሌ​ዋ​ው​ያ​ኑም አለ​ቆች አሳ​ብያ፥ ሰር​ብያ፥ ኢያሱ፥ የቀ​ድ​ም​ኤ​ልም ልጆች፥ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው እንደ ዳዊት ትእ​ዛዝ በየ​ሰ​ሞ​ና​ቸው በእ​ነ​ርሱ ፊት ያከ​ብ​ሩና ያመ​ሰ​ግኑ ነበር።


የበደለኛ ሰው በደሉ ሁሉ ወደ ጕያው ይመለሳል። ጽድቅ ሁሉ ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።


አሮ​ንም በሁ​ለቱ የፍ​የል ጠቦ​ቶች ላይ ዕጣ ይጥ​ል​ባ​ቸ​ዋል፤ አን​ዱን ዕጣ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ሌላ​ው​ንም ዕጣ ለሚ​ለ​ቀቅ።


ዕጣም አጣ​ጣ​ሏ​ቸው፤ ዕጣ​ዉም በማ​ት​ያስ ላይ ወጣ፤ ከዐ​ሥራ አንዱ ሐዋ​ር​ያት ጋራም ተቈ​ጠረ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos