Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 26:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ለሹፒምና ለሖሳ በምዕራብ በኩል የሚገኘው ቅጽር በርና በላይኛው መንገድ በኩል የሚገኘው ሻሌኬት ተብሎ የሚጠራው ቅጽር በር ደረሳቸው፤ የዘብ ጥበቃው አገልግሎት በክፍለ ጊዜ የተመደበ ሆኖ ቅደም ተከተል ተራ የያዘ ነበር፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 የምዕራቡ በርና በላይኛው መንገድ ላይ የሚገኘው የሸሌኬት በር ዕጣዎች ለሰፊንና ለሖሳ ወጣ። በአንዱ ዘብ ጥበቃ ትይዩ ሌላ ዘብ ጥበቃ ነበረ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ለሰፊንና ለሖሳ በዐቀበቱም መንገድ ባለው በሸሌኬት በር በምዕራብ በኩል ዕጣ ወጣላቸው፤ ይህም ጥበቃ ከጥበቃ ትይዩ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ለሶ​ፊ​ምና ለሖ​ሳም በም​ዕ​ራብ በኩል በዐ​ቀ​በቱ መን​ገድ ባለው በሸ​ለ​ኬት በር በኩል ጥበቃ በጥ​በቃ ላይ ዕጣ ወጣ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ለሰፊንና ለሖሳ በምዕራብ በኩል፥ በዐቀበቱም መንገድ ባለው በሸሌኬት በር በኩል በጥበቃ ላይ ጥበቃ ዕጣ ወጣባቸው።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 26:16
8 Referencias Cruzadas  

በሰሎሞን ገበታ ላይ የሚቀርበውን የምግብ ዐይነት፥ የመኳንንቱን መኖሪያ አካባቢዎች፥ የቤተ መንግሥቱን ሠራተኞች የሥራ አደረጃጀት፥ የደንብ ልብሳቸውንም ዐይነት፥ በግብዣ ጊዜ የሚያገለግሉትን አሳላፊዎችና በቤተ መቅደስም የሚያቀርባቸውን መሥዋዕቶችን ሁሉ ተመለከተች፤ በዚህም ሁሉ የተሰማት አድናቆት ከጠበቀችው በላይ ነበር።


የሥራ ምድባቸውን ለመወሰን ወጣት ሆነ ሽማግሌ፥ አስተማሪም ሆነ ተማሪ ለማንም ልዩነት ሳይደረግ ዕጣ ይጣጣሉ ነበር።


ለዖቤድኤዶም በደቡብ በኩል የሚገኘው ቅጽር በር ደረሰው፤ ልጆቹም የዕቃ ግምጃ ቤቶችን ለመጠበቅ ተመደቡ፤


በየቀኑ በምሥራቅ በኩል ስድስት፥ በሰሜን አራት፥ በደቡብ አራት ዘብ ጠባቂዎች ይመደባሉ፤ እንዲሁም በየቀኑ አራት ዘብ ጠባቂዎች የዕቃ ግምጃ ቤቶቹን ለመጠበቅ ሲመደቡ፥ ከእነርሱ ሁለቱ አንዱን የዕቃ ግምጃ ቤት፥ ሁለቱ ደግሞ ሌላውን ይጠብቁ ነበር።


በምዕራብ በኩል መንገዱን ተጠግቶ በተሠራው አደባባይ አጠገብ አራት ዘብ ጠባቂዎች ሲመደቡ፥ ራሱን አደባባዩን የሚጠብቁ ሁለት ዘብ ጠባቂዎች ተመድበው ነበር።


በሰሎሞን ገበታ ላይ የሚቀርበውን የምግብ ዐይነት፥ የመኳንንቱ አቀማመጥ፥ የቤተ መንግሥቱን ሠራተኞች የሥራ አደረጃጀት፥ የመጠጥ አሳላፊዎቹ የደንብ ልብስ ዐይነት፥ በግብዣ ጊዜ የሚያገለግሉትን አሳላፊዎችና በቤተ መቅደስም የሚያቀርባቸውን መሥዋዕቶች ሁሉ ተመለከተች፤ በዚህም ሁሉ የተሰማት አድናቆት ከጠበቀችው በላይ ነበር።


ሌዋውያኑ በሐሻብያ፥ በሼሬብያ፥ በኢያሱ፥ በቢኑይና በቃድሚኤል መሪነት በሁለት ቡድኖች ተከፈሉ። ሁለቱም ቡድኖች የእግዚአብሔር ሰው የሆነ ንጉሥ ዳዊት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት እየተቀባበሉ የምስጋና መዝሙር በማቅረብ እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos