“ነገር ግን በእውነት እግዚአብሔር በምድር ላይ ከሰዎች ጋር ይኖራልን? እነሆ፥ ሰማይ፥ ከሰማያትም በላይ ያለ ሰማይ ይይዝህ ዘንድ አይችልም፤ ይልቁንስ እኔ የሠራሁት ቤትማ ምንኛ ያንስ?
መዝሙር 68:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ ወደ ላይ ወደ መኖሪያህ በወጣህ ጊዜ ምርኮን ይዘህ ሄድክ፤ ከዐመፀኞች እንኳ ሳይቀር ከሰዎች ሁሉ ምርኮን ተቀበልክ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ላይ ዐረግህ፤ ምርኮ አጋበስህ፤ እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፤ አንተ በዚያ ትኖር ዘንድ፣ ከዐመፀኞችም ሳይቀር፣ ከሰዎች ስጦታን ተቀበልህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእግዚአብሔር ሠረገላዎች የብዙ ብዙ ሺህ ናቸው፥ ጌታ በመቅደሱ በሲና በመካከላቸው ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነፍሴን ተመልክተህ ተቤዣት፤ ስለ ጠላቶችም አድነኝ። |
“ነገር ግን በእውነት እግዚአብሔር በምድር ላይ ከሰዎች ጋር ይኖራልን? እነሆ፥ ሰማይ፥ ከሰማያትም በላይ ያለ ሰማይ ይይዝህ ዘንድ አይችልም፤ ይልቁንስ እኔ የሠራሁት ቤትማ ምንኛ ያንስ?
ክፉዎች አካሄዳቸውን፥ ኃጢአተኞች ክፉ ሐሳባቸውን ይተዉ፤ ምሕረቱ ብዙ ስለ ሆነ ይቅር ይላቸው ዘንድ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ይመለሱ።
ከፍተኛውና ከሁሉ የላቀው፥ ለዘለዓለም የሚኖር ቅዱሱ እንዲህ ይላል፦ “እኔ በተቀደሰና በከፍተኛ ቦታ፥ እንዲሁም ልባቸው ከተሰበረና መንፈሳቸው ትሑት ከሆኑት ጋር እኖራለሁ፤ ይኸውም ትሑት መንፈሳቸውንና የተሰበረ ልባቸውን ለማደስ ነው።
በአራቱም አቅጣጫ ያሉት የከተማይቱ የቅጽር ግንቦች ጠቅላላ ርዝመት ዐሥራ ስምንት ሺህ ክንድ ይሆናል፤ ከአሁን በኋላ የከተማይቱ መጠሪያ ስም “እግዚአብሔር በዚያ አለ!” የሚል ይሆናል።
እግዚአብሔር እንደ ነጐድጓድ ያለ ድምፁን በሠራዊቱ ላይ ያሰማል፤ ሠራዊቱ ምንኛ ብዙ ነው! ትእዛዙን የሚቀበሉ ከቊጥር በላይ ናቸው፤ በእርግጥም የእግዚአብሔር ቀን ታላቅ ነው፤ በጣም አስፈሪ ስለ ሆነ በዚያ ቀን ማን ችሎ ይቆማል?
ሂዱ፤ ‘እኔ የምፈልገው ምሕረትን እንጂ መሥዋዕትን አይደለም’ ተብሎ የተጻፈው ምን ማለት እንደ ሆነ መርምራችሁ አስተውሉ። እኔ የመጣሁት ጻድቃንን ሳይሆን ኃጢአተኞችን ወደ ንስሓ ለመጥራት ነው” አላቸው።
እኔ ግን እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ፤ የእኔ መሄድ ለእናንተ ይጠቅማችኋል፤ እኔ ካልሄድኩ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣም፤ እኔ ከሄድኩ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ።
እርሱም ራሱ እግዚአብሔር አስቀድሞ ባቀደውና ባወቀው አሠራር መሠረት ለእናንተ ተላልፎ ተሰጠ፤ እናንተም በዐመፀኞች እጅ እንዲሰቀልና እንዲሞት አደረጋችሁት።
ስለዚህ ሐናንያ ወደዚያ ሄዶ እርሱ ወደ ነበረበትም ቤት ገባ፤ እጁንም በሳውል ላይ ጭኖ፥ “ወንድሜ ሳውል ሆይ! ወደዚህ ስትመጣ ሳለ በመንገድ የተገለጠልህ ጌታ ኢየሱስ እንደገና ማየት እንድትችልና መንፈስ ቅዱስም እንዲሞላብህ ወደ አንተ ልኮኛል” አለው።
ነገር ግን እኛ ኃጢአተኞች ሆነን ሳለ ክርስቶስ በእኛ ምትክ ሞቶአል፤ ይህም እግዚአብሔር ለእኛ ያለው ፍቅር ምን ያኽል ታላቅ መሆኑን ያስረዳል።
የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ከጣዖቶች ጋር ምን ስምምነት አለው? እግዚአብሔርም፦ “መኖሪያዬን በሕዝቤ መካከል አደርጋለሁ፤ ከእነርሱም ጋር እኖራለሁ፤ እኔ አምላካቸው እሆናለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ” ብሎ እንደ ተናገረው እኛ እያንዳንዳችን የሕያው እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነን።
ሙሴም እንዲህ አለ፦ “እግዚአብሔር ከሲና ተራራ መጣ፤ ከኤዶም ላይ እንደ ንጋት ፀሐይ አበራ፤ ከፋራንም ተራራ ላይ አንጸባረቀ፤ በስተቀኙ የእሳት ነበልባል ነበር፤ ከእርሱም ጋር አእላፍ መላእክት ነበሩ።
እርሱ የእግዚአብሔር ክብር ነጸብራቅ ነው፤ እርሱ በባሕርዩ ከእግዚአብሔር ጋር ፍጹም ትክክል ነው። በኀያል ቃሉ ዓለምን ሁሉ ደግፎ ይዞአል፤ ሰዎችንም ከኃጢአት ካነጻ በኋላ በሰማይ በኀያሉ እግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦአል።
እንግዲህ ሰማያትን ዘልቆ ወደ ላይ ወደ ሰማይ የወጣ ታላቅ የካህናት አለቃ ስላለን እምነታችንን አጥብቀን እንያዝ፤ የካህናት አለቃውም የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ነው።
እንግዲህ ከምንነጋገርባቸው ነገሮች ዋናው ነገር ይህ ነው፤ በሰማይ በልዑል እግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ እንዲህ ያለ የካህናት አለቃ አለን፤
በቀኝ እጄ ያየሃቸው የሰባቱ ኮከቦችና የሰባቱም የወርቅ መቅረዞች ምሥጢር ይህ ነው፤ ሰባቱ ኮከቦች የሰባቱ አብያተ ክርስቲያን መላእክት ናቸው፤ ሰባቱ መቅረዞችም ሰባት አብያተ ክርስቲያን ናቸው።”
እንዲህም የሚል ከፍተኛ ድምፅ ከዙፋኑ ሲወጣ ሰማሁ፤ “እነሆ! የእግዚአብሔር ማደሪያ ከሰዎች ጋር ነው፤ ከእነርሱም ጋር ይኖራል፤ እነርሱም የእርሱ ሕዝብ ይሆናሉ። እግዚአብሔር ራሱ ከእነርሱ ጋር ይሆናል፤ አምላካቸውም ይሆናል፤