ስለዚህ እግዚአብሔር ከአባቴ ቤት ወጥቼ ወደ ባዕድ አገር እንድሄድ ባዘዘኝ ጊዜ ‘በምንሄድበት ቦታ ሁሉ እኅቱ ነኝ ብትዪ ለእኔ ታላቅ ውለታ እንዳደረግሽልኝ እቈጥረዋለሁ’ ብዬአት ነበር።”
መዝሙር 64:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክፉ ሤራ ለማቀነባበር እርስ በርሳቸው ይመካከራሉ፤ ወጥመዳቸውንም የት እንደሚዘረጉ ያቅዳሉ፤ ይህን ሁሉ ሲያደርጉ “ማንም ሊያየን አይችልም” ይላሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፉ ተግባር ለማከናወን እርስ በርስ ይመካከራሉ፤ በስውር ወጥመድ ለመዘርጋት ይነጋገራሉ፤ “ማንስ ሊያየን ይችላል?” ይባባላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጹሕንም በስውር ለመንደፍ ቀስትን ገተሩ፥ ድንገት ይነድፉታል አይፈሩምም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቤተ መቅደስህ ቅዱስ ነው በጽድቅም ድንቅ ነው። በምድር ዳርቻ ሁሉና በሩቅ ባሕር ውስጥ ላሉ ተስፋቸው የሆንህ፥ አምላካችንና መድኃኒታችን ሆይ ስማን። |
ስለዚህ እግዚአብሔር ከአባቴ ቤት ወጥቼ ወደ ባዕድ አገር እንድሄድ ባዘዘኝ ጊዜ ‘በምንሄድበት ቦታ ሁሉ እኅቱ ነኝ ብትዪ ለእኔ ታላቅ ውለታ እንዳደረግሽልኝ እቈጥረዋለሁ’ ብዬአት ነበር።”
እርሱም እንዲህ አለኝ፦ “የእስራኤል መሪዎች በየራሳቸው ጣዖት ቤት በጨለማ ሆነው እግዚአብሔር አያየንም! ምድሪቱንም ትቶአታል በማለት የሚያደርጉትን ታያለህን?” አለኝ።
የሕዝቡም ቊጥር ከእኛ እጅግ የበዛ ነው፤ ስለዚህ ወደዚህ መጥተህ እነርሱን ርገምልኝ፤ በዚህ ዐይነት ምናልባት ድል ልነሣቸውና ከምድሪቱ ላስወጣቸው እችል ይሆናል፤ አንተ የምትመርቀው የተመረቀ፥ አንተም የምትረግመው የተረገመ እንደሚሆን ዐውቃለሁ።”
“እናንተ ግብዞች፥ የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን! ወዮላችሁ! አንድን ሰው የእምነታችሁ ተከታይ ለማድረግ በባሕርና በየብስ ትዞራላችሁ፤ ባስገባችሁትም ጊዜ፥ ከእናንተ በሁለት እጥፍ ይብስ ለገሃነም የተዘጋጀ ታደርጉታላችሁ!
እነዚህ ሁለቱ ነቢያት የምድር ሰዎችን አስጨንቀው ስለ ነበረ በምድር የሚኖሩ ሰዎች በነቢያቱ ሞት ደስ ይላቸዋል፤ በደስታም በዓል ያደርጋሉ፤ ስጦታም ይለዋወጣሉ።