መዝሙር 58:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ እንደ እባብ መርዘኞች ናቸው፤ እንደ ደንቆሮ እፉኝትም ጆሮአቸውን ይደፍናሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መርዛቸው እንደ እባብ መርዝ ነው፤ አልሰማ ብላ ጆሮዋን እንደ ደፈነች እፉኝት ናቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክፉዎች ከማኅፀን ጀምረው ተለዩ፥ ከሆድም ጀምረው ሳቱ፥ ሐሰትንም ተናገሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያለ በደል ሮጥሁ ተዘጋጀሁም፤ ተነሥ፥ ተቀበለኝ፥ እይም። |
የመሥዋዕቱም መዓዛ እግዚአብሔርን ደስ አሰኘው፤ በሐሳቡም እንዲህ አለ፥ ገና ከሕፃንነቱ ጊዜ ጀምሮ የሰው ሐሳብ ክፉ መሆኑን ስለማውቅ፤ “ሰው በሚፈጽመው በደል ሁሉ ከእንግዲህ ወዲህ ምድርን አልረግምም፤ በአሁኑ ጊዜ እንዳደረግሁት ሕይወት ያለውን ፍጥረት ሁሉ ከእንግዲህ ወዲህ ከቶ አላጠፋም።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ተጠንቀቁ! እነሆ የአስማተኛ ድግምት ሊገታቸው የማይችል መርዘኛ እባቦችንና እፉኝቶችን በመካከላችሁ እልካለሁ፤ እነርሱም ይነድፉአችኋል።”
ነገር ግን፥ ዮሐንስ ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ብዙዎች ለመጠመቅ ወደ እርሱ ሲመጡ ባየ ጊዜ፥ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ የእባብ ልጆች! ከሚመጣው ቊጣ እንድታመልጡ ማን አስጠነቀቃችሁ?
ሰውን የሚጐዳ ክፉ ቃል ለመናገር አፋቸው እንደ መቃብር የተከፈተ ነው፤ በምላሳቸው ያታልላሉ፤ የከንፈራቸውም ንግግር እንደ እባብ መርዝ የሚጐዳ ነው፤