መዝሙር 47:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ ሕዝቦች ጸጥ ብለው እንዲገዙልንና መንግሥታትም በቊጥጥራችን ሥር እንዲሆኑ አደረገ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕዝቦችን ከእኛ በታች አደረገ፤ መንግሥታትንም ከእግራችን ሥር አስገዛልን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ልዑል ግሩምም ነውና፥ በምድር ሁሉ ላይም ታላቅ ንጉሥ ነውና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በተቀበሏት ጊዜ እግዚአብሔር በረከትዋን ያውቃል |
የመንግሥታት ሁሉ ንጉሥ ስለ ሆንክ አንተን የማይፈራ ማን ነው? በአሕዛብ ጠቢባንም ሆነ በንጉሦቻቸው መካከል አንተን የሚመስል ስለሌለ ክብር ይገባሃል።
እኔ ታላቅ ንጉሥ ነኝ፤ ስሜም በሕዝቦች ዘንድ የተከበረስለሆነ፥ ከበግ መንጋዎቹ መካከል አውራ በግ እያለው ለተሳለው ስለት ነውር ያለበትን በግ መሥዋዕት የሚያቀርብልኝ የተረገመ ነው!” ይላል የሠራዊት አምላክ።
እስራኤል ሆይ! የእርዳታህ ጋሻ፥ የድልህ ሰይፍ መዳንን ከእግዚአብሔር ያገኘ፥ እንዳንተ ያለ ሕዝብ ከቶ የለም፤ ምንኛ የታደልክ ነህ! ጠላቶች እየተለማመጡ ወደ አንተ ሲመጡ ጀርባቸውን ትረግጣለህ።
እርሱ ይህን የተዋረደውን ሰውነታችንን በመለወጥ የእርሱን ክቡር ሰውነት እንዲመስል ያደርገዋል፤ ይህንንም የሚያደርገው ሁሉን በሥልጣኑ ሥር ለማድረግ በሚያስችለው ኀይል ነው።
እግዚአብሔርም ለቀድሞ አባቶቻቸው በገባው ቃል መሠረት በአካባቢያቸው ሁሉ ሰላምን ሰጣቸው፤ በጠላቶቻቸው ላይ ብዙ ድልን አቀዳጅቶአቸው ስለ ነበረ ከጠላቶቻቸው አንድ እንኳ በፊታቸው ሊቆም አልቻለም።