ዳዊት፥ አኪጦፌል ከአቤሴሎም ጋር በዐመፅ መተባበሩን በሰማ ጊዜ “እግዚአብሔር ሆይ! የአኪጦፌልን ምክር ወደ ከንቱነት እንድትለውጥበት እለምንሃለሁ!” ሲል ጸለየ።
መዝሙር 43:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላክ ሆይ! ፍረድልኝ፤ በአንተ ከማያምኑ አሕዛብ ፊት ስለ እኔ ተከራከርልኝ፤ ከአታላዮችና ከክፉ ሰዎችም እጅ አድነኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላክ ሆይ፤ ፍረድልኝ፤ ካልታመኑህ ሕዝብ ጋራ ተሟገትልኝ፤ ከአታላዮችና ከክፉዎች ሰዎችም አድነኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ ፍረድልኝ፥ ከጽድቅ በራቁም ሕዝብ ዘንድ ተሟገትልኝ፥ ከሸንጋይና ከግፈኛ ሰው አድነኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ በጆሮአችን ሰማን፥ አባቶቻችንም በዘመናቸው በቀድሞ ዘመን የሠራኸውን ሥራ ነገሩን። |
ዳዊት፥ አኪጦፌል ከአቤሴሎም ጋር በዐመፅ መተባበሩን በሰማ ጊዜ “እግዚአብሔር ሆይ! የአኪጦፌልን ምክር ወደ ከንቱነት እንድትለውጥበት እለምንሃለሁ!” ሲል ጸለየ።
ከዚህ በኋላ አቤሴሎም ወደ አኪጦፌል መለስ ብሎ “እነሆ እኛ አሁን በዚህ ተገኝተናል፤ ታዲያ ምን እንድናደርግ ትመክረናለህ?” ሲል ጠየቀው።
እግዚአብሔርን በድዬዋለሁ፤ ስለዚህም እርሱ የቀረበብኝን ክስ ተመልክቶ እስኪፈርድልኝ ድረስ ቊጣውን እታገሣለሁ፤ በመጨረሻም እርሱ ወደ ብርሃን ያወጣኛል፤ ፍትሕንም ይሰጠኛል።
እግዚአብሔር ይፍረድ፤ ከሁለታችንም ስሕተተኛው ማን እንደ ሆነ እርሱ ይወስን፤ እግዚአብሔር ይህን ጉዳይ ተመልክቶ ይከላከልልኝ፤ ከአንተም እጅ ያድነኝ።”