ይሁን እንጂ እንዲህ በማለት የተስፋ ቃል ሰጥቶኛል፥ ‘እኔ ከጠላቶቹ ሁሉ አሳርፌ ሰላም ስለምሰጠው በሰላም የሚያስተዳድር ወንድ ልጅ ይኖርሃል፤ በእርሱ ዘመነ መንግሥት ለእስራኤል ሰላምና ጸጥታ ስለምሰጥ ስሙ ሰሎሞን ተብሎ ይጠራል፤
መዝሙር 147:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ ወሰንሽን በሰላም ይጠብቃል፤ በመልካም ስንዴም ያጠግብሻል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በድንበርሽ ውስጥ ሰላም ያሰፍናል፤ ማለፊያ ስንዴም ያጠግብሻል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በወሰንሽም ሰላምን አደረገ፥ የስንዴንም ስብ አጠገበሽ። |
ይሁን እንጂ እንዲህ በማለት የተስፋ ቃል ሰጥቶኛል፥ ‘እኔ ከጠላቶቹ ሁሉ አሳርፌ ሰላም ስለምሰጠው በሰላም የሚያስተዳድር ወንድ ልጅ ይኖርሃል፤ በእርሱ ዘመነ መንግሥት ለእስራኤል ሰላምና ጸጥታ ስለምሰጥ ስሙ ሰሎሞን ተብሎ ይጠራል፤
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሀብትዋን እንደ ወንዝ ውሃ አበዛዋለሁ፤ የሕዝቦችንም ሀብት እንደ ወንዝ ጅረት አደርገዋለሁ፤ በክንድዋም ተይዛችሁ ትጠባላችሁ፤ በጭንዋም ላይ አድርጋ ትንከባከባችኋለች።
ከብርና ከወርቅ የተሠሩ ብዙ ጌጣጌጦች ነበሩሽ፤ ከልዩ ልዩ ሐር የተሠሩና በጥልፍ ጌጥ የተዋቡ ውድ ልብሶች ነበሩሽ፤ ምርጥ ከሆነ ዱቄት የተጋገረ ዳቦ፥ ማርና የወይራ ዘይት ትመገቢ ነበር፤ ውበትሽ እጅግ እየጨመረ ስለ ሄደ ንግሥት ለመሆን በቃሽ።
“በምድራችሁ ሰላምን እሰጣችኋለሁ፤ ማንንም ሳትፈሩ ያለ ስጋት ትተኛላችሁ፤ አደገኞች የሆኑ አራዊትን ከምድራችሁ አስወግዳለሁ፤ ከእንግዲህም ወዲህ ጦርነት በዚያ አይኖርም።
ከዚህ በኋላ ምድሬን ዙሪያዋን ከብቤ እጠብቃለሁ፤ የወራሪ ኀይል መተላለፊያም አላደርጋትም። ሕዝቤ ምን ያኽል እንደ ተሠቃየ ስለ ተመለከትኩ ከእንግዲህ ወዲህ ጨቋኞች አይወሩአቸውም።”
ከከብቶች፥ ከበጎችና ከፍየሎች መንጋ በሚገኝ ወተትና ዕርጎ፥ ከባሳን በሚገኙ ምርጥ ጠቦቶች፥ አውራ በጎች፥ ኰርማዎችና ፍየሎች ጮማ ሥጋ ከምርጥ ስንዴ ዳቦ ጋር መገባቸው። እናንተም ሕዝቦቹ ከቀይ ወይን ዘለላ ጭማቂ የወይን ጠጅ ጠጣችሁ።