Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 147:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እርሱ የበሮችሽን መወርወሪያ አጠንክሮ ይጠብቃል፤ በውስጥሽ ያሉትንም ሕዝቦችሽን ይባርካል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 እርሱ የደጆችሽን መወርወሪያ አጽንቷልና፤ ልጆችሽንም በውስጥሽ ባርኳል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 የደጆችሽን መወርወሪያ አጽንቶአልና፥ ልጆችንም በውስጥሽ ባርኮአልና።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 147:13
20 Referencias Cruzadas  

ካህናቱና ሌዋውያኑም ስለ ሕዝቡ ራሳቸው ስለ ከተማይቱ በሮችና ስለ ቅጽሩ የማንጻትን ሥርየት ፈጸሙ።


ሰንባላጥ፥ ጦቢያ፥ ዐረባዊው ጌሼምና ሌሎችም ጠላቶቻችን የቅጽሩን ግንብ ሠርቼ መፈጸሜንና ያልተሠራ ክፍት ቦታ አለመኖሩን ሰሙ፤ ይሁን እንጂ በቅጽር በሮቹ ላይ መዝጊያዎችን አላቆምኩም ነበር።


እነሆ የቅጽሩ ግንብ ተሠርቶ አለቀ፤ የቅጽር በሮችም ሁሉ በየቦታቸው ተገጣጥመው ነበር፤ ቤተ መቅደሱን የሚጠብቁ ዘበኞች ለመዘምራን ቡድን አባላትና ለሌሎችም ሌዋውያን የሥራ ድርሻቸው ተመድቦላቸው ነበር።


ለእነርሱም የሰጠኋቸው መመሪያ የኢየሩሳሌም የቅጽር በሮች ፀሐይ እስኪሞቅ ድረስ እንዳይከፈቱ፥ ደግሞ ማታ ፀሐይ ስትጠልቅ የዘብ ጠባቂዎቹ ከመሄዳቸው በፊት የቅጽር በሮቹ በቊልፍና በመወርወሪያ አጥብቀው እንዲዘጉአቸው ነበር። እንዲሁም ከኢየሩሳሌም ነዋሪዎች መካከል ሰዎችን ቀጥረው ከፊሎቹ በሥራቸው ላይ ሆነው ሌሎቹ ደግሞ በየቤታቸው ፊት ለፊት ሆነው እንዲጠብቁ አዘዝኳቸው።


ተራራዎች በኢየሩሳሌም ዙሪያ እንደ ሆኑ እንዲሁም ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም እግዚአብሔር በሕዝቡ ዙሪያ ነው።


ወንዶች ልጆቻችን በወጣትነታቸው ጊዜ እንደ አዲስ ተክል የሚያድጉና የሚጠነክሩ ይሁኑ፤ ሴቶች ልጆቻችን ለቤተ መንግሥት ማእዘኖች ውበት እንደሚሰጡ፥ ተቀርጸው ቀጥ እንዳሉ ምሰሶች ይሁኑ።


አምላክ ሆይ! ጽዮንን ለመርዳት፥ የኢየሩሳሌምን ቅጥሮች ለመገንባት እባክህ ፈቃድህ ይሁን።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ኤርምያስ ሆይ! ‘ይህች ምድር ሰዎችም ሆኑ እንስሶች የማይኖሩባት ባድማ ነች’ ያልከው አባባል ለጊዜው ትክክል ነው፤ የይሁዳ ከተሞችና የኢየሩሳሌም መንገዶች ምንም ሰዎች ወይም እንስሶች የማይታዩባት ባድማ ነች፤ አንድ ቀን ግን በዚህ ቦታ የተድላና የደስታ ድምፅ ይሰማል፤


በዚህ ቦታ የተድላና የደስታ፥ የሠርግ ዘፈን ድምፅ እንደገና ይሰማል፤ ከምርኮ ለተመለሱትም ቀድሞ የነበራቸውን ንብረታቸውን ስለምመልስላቸው የምስጋና መሥዋዕት ለማቅረብ ወደ ቤተ መቅደሴ በሚመጡበት ጊዜ፥ ‘የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ እርሱ ቸር ነውና፥ ፍቅሩም ዘለዓለማዊ ነውና’ እያሉ በከፍተኛ ድምፅ ይዘምራሉ። ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”


የምድር ነገሥታትም ሆኑ የዓለም ሕዝቦች በኢየሩሳሌም የቅጽር በሮች ጠላት ይገባል ብለው አላመኑም።


ይህን ልብ ብለህ አስተውል፤ ኢየሩሳሌም እንድትታደስ ትእዛዝ ከወጣበት ጊዜ አንሥቶ መሲሕ እስከሚመጣበት ጊዜ ድረስ ሰባት ሳምንቶች ያልፋሉ፤ እንዲሁም ለሥልሳ ሁለት ሳምንት በችግር ጊዜ ኢየሩሳሌም፥ መንገዶችዋና የመከላከያ ጒድጓድዋ ይገነባሉ። ይሁን እንጂ ይህ ሁሉ የመከራ ዘመን ይሆናል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos