መዝሙር 143:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዘለዓለማዊ ፍቅርህን ግለጥልኝ፤ ጠላቶቼን አጥፋቸው፤ እኔ አገልጋይህ ስለ ሆንኩ ጥቃት የሚያደርሱብኝን ሁሉ ደምስሳቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጠላቶቼንም ለእኔ ስላለህ ምሕረት ደምስሳቸው፤ እኔ ባሪያህ ነኝና፣ ነፍሴን የሚያስጨንቋትን ሁሉ አጥፋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጽኑ ፍቅርህ ጠላቶቼን ደምስሳቸው፥ እኔ ባርያህ ነኝና ነፍሴን የሚያስጨንቁአትን ሁሉ አጥፋቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልጆቻቸው በጐልማስነታቸው እንደ አዲስ ተክል የሆኑ፥ ሴቶች ልጆቻቸውም እንደ እልፍኝ ያማሩና ያጌጡ፤ |
አምላክ ሆይ! አንተ ግን ክፉዎችን ወደ ጥልቅ ጒድጓድ ትጥላቸዋለህ፤ እነዚያ ነፍሰ ገዳዮችና ከዳተኞች ግማሽ ዕድሜአቸውን እንኳ አይኖሩም፤ እኔ ግን በአንተ እተማመናለሁ።
ማንም ሰው በአንተ ላይ አደጋ ጥሎ ሊገድልህ ቢፈልግ አንድ ሰው ውድ የሆነ ሀብቱን እንደሚጠብቅ አምላክህ እግዚአብሔር አንተን በሰላም ይጠብቅሃል፤ ስለ ጠላቶችህም የሆነ እንደ ሆነ አንድ ሰው ድንጋዩን ከወንጭፍ እንደሚያስፈነጥር እግዚአብሔር ራሱ አሽቀንጥሮ ይጥላቸዋል።
በሕያው እግዚአብሔር ስም እምልልሃለሁ፤ እግዚአብሔር ራሱ ሳኦልን ይገድለዋል፤ የሚሞትበት ጊዜ ደርሶ፥ አለበለዚያም በጦርነት መሞቱ አይቀርም፤