የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! ለአባቴ ለዳዊት ‘አንተ ሕጌን በጥንቃቄ እንደ ጠበቅህ ልጆችህም ቢጠብቁ፥ ከዘርህ መካከል በእስራኤል ላይ በፊቴ የሚነግሥ ዘወትር ይኖራል’ በማለት የገባህለትን ቃል ኪዳን አሁን እንድታጸናልኝ እለምንሃለሁ፤
መዝሙር 119:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወጣቶች ሕይወታቸውን በንጽሕና መጠበቅ የሚችሉት ትእዛዞችህን በመፈጸም ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጕልማሳ መንገዱን እንዴት ያነጻል? በቃልህ መሠረት በመኖር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጎልማሳ መንገዱን በምን ያነጻል? ቃልህን በመጠበቅ ነው። |
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! ለአባቴ ለዳዊት ‘አንተ ሕጌን በጥንቃቄ እንደ ጠበቅህ ልጆችህም ቢጠብቁ፥ ከዘርህ መካከል በእስራኤል ላይ በፊቴ የሚነግሥ ዘወትር ይኖራል’ በማለት የገባህለትን ቃል ኪዳን አሁን እንድታጸናልኝ እለምንሃለሁ፤
የግብዣዎቹ ቀኖች ከተፈጸሙ በኋላ ኢዮብ በማለዳ ተነሥቶ ልጆቹን ያስጠራና በእያንዳንዱ ልጁ ስም መሥዋዕት ያቀርብ ነበር፤ ይህንንም የሚያደርገው “ምናልባት ከልጆቼ አንዱ እግዚአብሔርን በመስደብ በድሎ ይሆናል!” በሚል ስጋት ልጆቹን ከኃጢአት ለማንጻት ነበር። ኢዮብ ይህን ሥርዓት ሳያቋርጥ ዘወትር ይፈጽም ነበር።
ወጣት ሆይ! ወጣትነት እጅግ ግሩም ስለ ሆነ በወጣትነትህ ዘመን ደስ ይበልህ፤ በልብህም ሐሤት አድርግ፤ ዐይንህ የሚያየውንና ልብህ የሚመኘውን ሁሉ ፈጽም፤ ሆኖም ስለዚህ ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ወደ ፍርድ እንደሚያመጣህ ዕወቅ።
ይልቅስ ንጉሥ በሚሆንበት ጊዜ እነዚህ በሌዋውያን ካህናት ተጠብቀው የሚኖሩት የእግዚአብሔር ሕግጋት የተጻፉበትን መጽሐፍ አንድ ቅጅ እንዲኖረው ያድርግ።
አንተ ብቻ አይዞህ፤ በርታ፤ አገልጋዬ ሙሴ ለሰጠህም ሕግ ሁሉ እውነተኛ ታዛዥ ሁን፤ በምትሄድበት ስፍራ ሁሉ ማናቸውም ነገር እንዲሳካልህ ከዚህ ሕግ ከቶ ዝንፍ አትበል፤