8 ሕግህን ስለምፈጽም ፈጽሞ አትተወኝ።
8 ሥርዐትህን እጠብቃለሁ፤ ፈጽመህ አትተወኝ።
8 ሥርዓትህን እጠብቃለሁ፥ በፍጹም አትጣለኝ።
አሁንም በእርጅናዬ ዘመን አትጣለኝ፤ ደካማ በምሆንበትም ጊዜ አትተወኝ።
ኀይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን ነገር ማድረግ እችላለሁ።
ከፊትህ አታርቀኝ፤ ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ አትውሰድብኝ።
እንደ ጠፋ በግ ተቅበዝብዤአለሁ፤ ነገር ግን ትእዛዞችህን ስላልረሳሁ፥ እኔን አገልጋይህን ፈልገኝ።
አምላክ ሆይ! ሥልጣንህን ለሚመጣው ትውልድ፥ ኀይልህንም ለሚመጡት ሁሉ እስክገልጥና አርጅቼ እስክሸብት ድረስ እንኳ አትተወኝ።
እውነተኛ ትእዛዞችህን ለመጠበቅ በመሐላ የገባሁትን ቃል አጸናለሁ።
በሕግህ ደስ ይለኛል፤ ቃልህንም አልረሳም።
እርሱን ማምለክ መልካም መስሎ ካልታያችሁ ግን የቀድሞ አባቶቻችሁ ከኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ በነበሩበት ጊዜ ያመልኩአቸው የነበሩትን ወይም አሁን በምድራቸው የምትኖሩባቸውን የአሞራውያንን አማልክት ታመልኩ እንደሆን የምታመልኩትን ዛሬውኑ ምረጡ፤ እኔና ቤተሰቤ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን።”
እግዚአብሔር ሆይ! በሙሉ ልቤ፤ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ ስማኝ፤ እኔም ሕጎችህን እፈጽማለሁ።