11 አንተን እንዳልበድል ቃልህን በልቤ አኖራለሁ።
11 አንተን እንዳልበድል፣ ቃልህን በልቤ ሰወርሁ።
11 አንተን እንዳልበድል፥ ቃልህን በልቤ ሰወርሁ።
የአምላኩም ሕግ በልቡ ነው፤ እግሩም አይደናቀፍም።
የክርስቶስ ቃል በሙላት በልባችሁ ይኑር፤ በጥበብ ሁሉ እርስ በርሳችሁ ተማማሩ፤ ተመካከሩ፤ በመዝሙርና በውዳሴ፥ በመንፈሳዊ ዜማም እግዚአብሔርን ከልብ እያመሰገናችሁ ዘምሩ።
አምላኬ ሆይ! ፈቃድህን መፈጸም እወዳለሁ፤ ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው” አልኩ።
የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! እኔ በስምህ ተጠርቼአለሁ፤ ቃልህ ወደ እኔ በመጣ ጊዜ በሙሉ ተቀብዬዋለሁ፤ ልቤንም በደስታና በሐሴት ሞላው።
እንዲህ ያለው ሰው፥ በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል፤ ቀንና ሌሊትም ያሰላስለዋል።
እግዚአብሔር የሚሰጥህን ትምህርት ተቀበል፤ ቃሉንም በልብህ አኑር።
ሕግህን እጅግ እወዳለሁ፤ ስለ እርሱ ቀኑን ሙሉ አስባለሁ።
“እናንተ ትክክለኛውን ነገር የምታውቁና ሕጌ በልባችሁ ያለ ሰዎች አድምጡኝ፤ የሰዎችን ነቀፋ አትፍሩ፤ ወይም በስድባቸው አትደናገጡ።
ልጄ ሆይ! የማስተምርህን ተቀበል፤ ትእዛዞቼንም በልብህ አኑር።
ማርያም ግን፥ ይህን ሁሉ ነገር በልብዋ ይዛ ታሰላስለው ነበር።
ኃጢአት እንዳይሠለጥንብኝ ዐውቆ ከመበደል ጠብቀኝ፤ ይህም ከሆነ ታላቅ በደል ከመሥራት ንጹሕ እሆናለሁ።
ከዚያም በኋላ ኢየሱስ ከእነርሱ ጋር ወደ ናዝሬት ሄደ፤ ይታዘዛቸውም ነበር፤ እናቱም ይህን ሁሉ ነገር በልብዋ ትይዘው ነበር።