መዝሙር 103:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በግዛቱ ሁሉ የምትገኙ ፍጥረቶቹ እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ነፍሴ ሆይ! እግዚአብሔርን አመስግኚ! አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ በግዛቱ ሁሉ የምትኖሩ፣ ፍጥረቱ ሁሉ፣ እግዚአብሔርን ባርኩ። ነፍሴ ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኪ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፍጥረቶቹ ሁሉ በግዛቱ ስፍራ ሁሉ፥ ጌታን ባርኩ። ነፍሴ ሆይ፥ ጌታን ባርኪ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፀሐይ ስትወጣ ይገባሉ፥ በየዋሻቸውም ይውላሉ። |
ለተመረጡት ሕዝቤ ውሃን ለመስጠት ወንዞች በበረሓ ጅረቶች በምድረ በዳ እንዲፈስሱ ባደረግሁ ጊዜ የምድር አራዊት እንኳ ሳይቀሩ ያከብሩኛል፤ ቀበሮዎችና ሰጎኖችም ያመሰግኑኛል።
ሰማያት ሆይ! እግዚአብሔር ሕዝቡን እስራኤልን በማዳን ክብሩን ገልጦአልና በደስታ ዘምሩ፤ ምድርም ከታች እልል በዪ፤ ተራራዎች፥ ጫካዎችና በውስጣቸው የምትገኙ ዛፎች ሁሉ የደስታ ድምፅ እያሰማችሁ ፈንድቁ።