ምሳሌ 13:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ተጠንቅቆ የሚናገር ሕይወቱን ይጠብቃል። ግዴለሽ ተናጋሪ ግን ጥፋት ይደርስበታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንደበቱን የሚጠብቅ ሕይወቱን ይጠብቃል፤ አፉ እንዳመጣለት የሚናገር ግን ይጠፋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አፉን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃል፥ ከንፈሩን የሚያሞጠሙጥ ግን ጥፋት ያገኘዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አፉን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃል፤ በከንፈሩ የሚቸኩል ግን ራሱን ይጥላል። |
በመጨረሻ እውነቱን ነገራት፤ እንዲህም አላት፦ “ከተወለድኩበት ጊዜ ጀምሮ በናዝራዊነት ለእግዚአብሔር የተለየሁ ስለ ሆነ ጠጒሬ ተላጭቶ አያውቅም፤ ጠጒሬ ቢላጭ ግን ኀይል ተለይቶኝ እንደማንኛውም ሰው ደካማ እሆናለሁ።”