ዘኍል 20:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኛም ይረዳን ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጮኽን፤ እርሱም ጩኸታችንን ሰምቶ ከግብጽ የሚያወጣንን መልአክ ላከልን፤ እነሆ አሁን እኛ በግዛትህ ወሰን ላይ ባለችው በቃዴስ እንገኛለን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ እግዚአብሔር በጮኽን ጊዜ ግን ጩኸታችንን ሰማ፤ መልአክ ልኮም ከግብጽ አወጣን። “አሁንም ያለነው እዚሁ ቃዴስ በግዛትህ ድንበር ላይ ባለችው ከተማ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ጌታም በጮኽን ጊዜ ድምፃችንን ሰማ፥ መልአክንም ልኮ ከግብጽ አወጣን፤ እነሆም፥ በምድርህ ዳርቻ ባለችው ከተማ በቃዴስ ተቀምጠናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ እግዚአብሔርም ጮኽን፤ እግዚአብሔርም ድምፃችንን ሰማ፤ መልአክንም ልኮ ከግብፅ አወጣን፤ እነሆም፥ በምድርህ ዳርቻ ባለችው ከተማ በቃዴስ ተቀምጠናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ እግዚአብሔርም በጮኽን ጊዜ ድምፃችንን ሰማ፥ መልአክንም ሰድዶ ከግብፅ አወጣን፤ እነሆም፥ በምድርህ ዳርቻ ባለችው ከተማ በቃዴስ ተቀምጠናል። |
የእስራኤልን ሠራዊት ፊት ፊት ይመራ የነበረው የእግዚአብሔር መልአክ ወደ ኋላ ተመልሶ ደጀን ሆነ፤ የደመናውም ዐምድ አልፎ በኋላ በኩል ቆመ፤
ፊት ፊትህ እየሄደ የሚመራህ መልአክ እልካለሁ፤ ከነዓናውያንን፥ አሞራውያንን፥ ሒታውያንን፥ ፈሪዛውያንን፥ ሒዋውያንንና ኢያቡሳውያንን ከፊትህ አባርራለሁ።
እነሆ፥ አሁንም ግብጻውያን ባርያዎች አድርገው የሚያስጨንቁአቸውን የእስራኤላውያንን መራራ ጩኸት ሰምቼአለሁ፤ የገባሁትንም ቃል ኪዳን አስታውሼአለሁ።
አንበሶቹ እንዳይጐዱኝ እግዚአብሔር መልአኩን ልኮ አፋቸውን ዘጋ፤ ይህንንም ያደረገው እኔ በእርሱ ዘንድ ንጹሕ መሆኔንና አንተንም አለመበደሌን ስላወቀ ነው።”
የቀድሞ አባቶቻችን እንዴት ወደ ግብጽ እንደ ወረዱና እኛም በግብጽ ለብዙ ዓመቶች እንዴት እንደ ኖርን ታውቃለህ፤ ግብጻውያን የቀድሞ አባቶቻችንም ሆነ እኛን በብርቱ አሠቃይተዋል፤
“በምድርህ አልፈን እንድንሄድ ፍቀድልን፤ እኛና ከብቶቻችን ከመንገዱ አንወጣም፤ ወደ እርሻዎችህም ሆነ ወደ ወይን ተክሎችህ አንገባም፤ ከውሃ ጒድጓዶችህም ውሃ አንጠጣም፤ ከግዛትህ እስክንወጣ ድረስ ዋናውን መንገድ አንለቅም።”
ወይስ በፈተና፥ በተአምራትና በድንቅ ነገሮች፥ በጦርነት፥ በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ፥ በሚያስፈራ ኀይል፥ በዐይናችሁ እያያችሁት እግዚአብሔር አምላካችሁ እናንተን ከግብጽ ምድር እንዳወጣችሁ ያለ አንድን ሕዝብ ከሌላ ሕዝብ መካከል ወስዶ የራሱ ሕዝብ ለማድረግ የሞከረ ሌላ አምላክ አለን?