ማቴዎስ 25:40 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡም ‘በእውነት እላችኋለሁ፤ ከእነዚህ ከወንድሞቼ አነስተኛ ለሆነው ለአንዱ እንኳ ያደረጋችኹት ሁሉ ለእኔ እንዳደረጋችሁት ነው!’ ሲል ይመልስላቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ንጉሡም መልሶ፣ ‘እውነት እላችኋለሁ፣ ከእነዚህ አነስተኛ ከሆኑት ወንድሞቼ ለአንዱ ያደረጋችሁት፣ ለእኔ እንዳደረጋችሁት ነው’ ይላቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡም እንዲህ ሲል ይመልስላቸዋል ‘እውነት እላችኋለሁ፤ ከሁሉ ለሚያንሱት ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ያደረጋችሁት ለእኔ እንዳደረጋችሁት ነው።’ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም መልሶ ‘እውነት እላችኋለሁ፤ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት፤’ ይላቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም መልሶ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት ይላቸዋል። |
ዳዊትም “አይዞህ አትፍራ! ስለ አባትህ ስለ ዮናታን ስል ቸርነት አደርግልሃለሁ፤ የአያትህ የሳኦል ይዞታ የነበረውን መሬት ሁሉ እመልስልሃለሁ፤ ዘወትርም በማእዴ ተቀምጠህ ትመገባለህ” አለው።
ስለዚህም በሰገነቱ ላይ አንድ ትንሽ ክፍል ሠርተን በዚያች ውስጥ አንድ አልጋ፥ አንድ ጠረጴዛ፥ አንድ ወንበርና አንድ የፋኖስ መብራት እናኑርለት፤ እርሱም እኛን ለመጐብኘት በሚመጣበት ጊዜ ሁሉ ማረፊያ ትሆነዋለች።”
በእውነት እላችኋለሁ፤ የእኔ ደቀ መዝሙር በመሆኑ፥ ከነዚህ ታናናሾች ለአንዱ አንድ ብርጭቆ ቀዝቃዛ ውሃ እንኳ የሚሰጥ ሰው ዋጋውን አያጣም።”
በዚያን ጊዜ ንጉሡ በቀኙ በኩል ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል፦ ‘እናንተ አባቴ የባረካችሁ! ኑ! ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ!
ንጉሡም ‘በእውነት እላችኋለሁ፤ ከእነዚህ ከወንድሞቼ አነስተኛ ለሆነው ለአንዱ እንኳ ያላደረጋችሁት ሁሉ ለእኔ እንዳላደረጋችሁት ነው’ ይላቸዋል።
ኢየሱስ “ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና አትንኪኝ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሂጂና ‘እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ፥ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዐርጋለሁ ብሎአል’ ብለሽ ንገሪያቸው” አላት።
ይህም የሆነበት ምክንያት አስቀድሞ ያወቃቸው ልጁን እንዲመስሉና ልጁም ከብዙ ወንድሞች መካከል በኵር እንዲሆን እግዚአብሔር አስቀድሞ ስለ ወሰነ ነው።
እኛ የምናስተምረው ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ መሆኑንና እኛም ራሳችን ስለ ኢየሱስ የእናንተ አገልጋዮች መሆናችንን ነው እንጂ ስለ ራሳችንስ አንሰብክም።
ወንድሞቼ ሆይ! እናንተ ለነጻነት ተጠርታችኋል፤ ነገር ግን አንዱ ሌላውን በፍቅር ያገልግል እንጂ ይህ ነጻነታችሁ የሥጋን ምኞት መፈጸሚያ ምክንያት አይሁን።
ለምእመናን ቅንነት የተሞላበት ፍቅር እንዲኖራችሁ ለእውነት በመታዘዝ ነፍሳችሁን አንጽታችኋል፤ ስለዚህ በሙሉ ልባችሁ እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ።
እነርሱ በበጉ ላይ ጦርነት ይከፍታሉ፤ ነገር ግን በጉ የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለ ሆነ ድል ይነሣቸዋል፤ ከእርሱ ጋር ያሉት የተጠሩ የተመረጡና የታመኑ ናቸው።”