እግዚአብሔርም ‘አክዓብ ወደ ራሞት ሄዶ በዚያ እንዲገደል ሊያሳስተው የሚችል ማነው?’ አለ፤ ከመላእክቱም መካከል አንዱ አንድ ነገር፥ ሌላው ሌላ ነገር በመግለጥ የተለያየ ሐሳብ ያቀርቡ ነበር፤
ዮሐንስ 12:40 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በዐይናቸው አይተውና በልባቸው አስተውለው እንዳይመለሱና እንዳይፈውሳቸው እግዚአብሔር ዐይናቸውን አሳውሮአል፤ ልባቸውንም አደንድኖአል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ዐይናቸውን አሳውሯል፤ ልባቸውንም አደንድኗል፤ ስለዚህ በዐይናቸው አያዩም፤ በልባቸውም አያስተውሉም፤ እንዳልፈውሳቸውም አይመለሱም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በዐይኖቻቸው እንዳያዩ፥ በልባቸውም እንዳያስተውሉ፥ እንዳይመለሱም፥ እኔም እንዳልፈውሳቸው፥ ዐኖቻቸውን አሳወረ፤ ልባቸውውንም አደነደነ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በዐይናቸው አይተው፥ በልባቸውም አስተውለው እንዳይመለሱና እንዳልፈውሳቸው ዐይኖቻቸው ታወሩ፤ ልባቸውም ደነደነ።” |
እግዚአብሔርም ‘አክዓብ ወደ ራሞት ሄዶ በዚያ እንዲገደል ሊያሳስተው የሚችል ማነው?’ አለ፤ ከመላእክቱም መካከል አንዱ አንድ ነገር፥ ሌላው ሌላ ነገር በመግለጥ የተለያየ ሐሳብ ያቀርቡ ነበር፤
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “እነሆ እንደገና ወደ ፈርዖን ተመልሰህ ግባ፤ እኔ የእርሱንና የመኳንንቱን ልብ ያደነደንኩት በመካከላቸው እነዚህን ተአምራት ለማድረግ ዐቅጄ ነው፤
ሙሴና አሮንም እነዚህን ተአምራት በንጉሡ ፊት አደረጉ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር የንጉሡን ልብ ስላደነደነ እስራኤላውያን ከምድሪቱ እንዲወጡ አልፈቀደላቸውም።
እኔም ልቡን ስለማደነድነው ያሳድዳችኋል፤ ስለዚህም በንጉሡና በሠራዊቱ ላይ የምጐናጸፈው ድል ለእኔ ክብር ይሆናል፤ በዚያን ጊዜ ግብጻውያን እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ያውቃሉ።” እስራኤላውያንም እንደ ተነገራቸው አደረጉ።
እንደገናም እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “እንግዲህ አሁን ወደ ግብጽ መመለስህ ስለ ሆነ፥ በሰጠሁህ ኀይል የምታደርጋቸውን ተአምራት በፈርዖን ፊት መፈጸም እንዳለብህ አትዘንጋ፤ ሆኖም እኔ የፈርዖንን ልብ ስለማደነድን ሕዝቡን በቀላሉ አይለቅም።
አምላክ ሆይ፥ ክንድህ ለመቅጣት ተነሥቶአል፤ አንተን የሚጠሉ ሰዎች አያዩትም፤ ለሕዝብህ ምን ያኽል ቅናት እንዳለህ አይተው ይፈሩ፤ ለጠላቶችህ ባዘጋጀኸው ቅጣት ይጥፉ።
እርሱ ግን ተወግቶ የቈሰለው ስለ መተላለፋችን ነው፤ የደቀቀውም ስለ በደላችን ነው፤ እኛ የዳንነው እርሱ በተቀበለው ቅጣት ነው፤ በእርሱም ቊስል እኛ ተፈወስን።
ቀጥሎም “እንዳያዩ፥ እንዳይሰሙና እንዳያስተውሉ በዓይናቸው ተመልክተው፥ በጆሮአቸው ሰምተው፥ በልባቸው አስተውለው ወደ እኔ ተመልሰው እንዳይፈወሱ ይህን ሕዝብ ልቡ የደነደነ፥ ጆሮው የተደፈነ፥ ዐይኑም የተጨፈነ እንዲሆን አድርግ” አለኝ።
እርሱም “እንግዲያውስ ወደዚህ ሕዝብ ሂድና ‘መስማትንስ ትሰማላችሁ፤ ነገር ግን አታስተውሉም፤ ማየትንም ታያላችሁ ነገር ግን ልብ አታደርጉም’ በላቸው” አለኝ።
እናንተ ከእግዚአብሔር ርቃችሁ የነበራችሁ ሁሉ ተመለሱ፤ እርሱ ይፈውሳችኋል፤ ታማኞችም ያደርጋችኋል። እናንተም እንዲህ ብላችኋል፦ “አዎ! እግዚአብሔር አምላካችን ስለ ሆነ ወደ እርሱ እንመለሳለን፤
“የሰው ልጅ ሆይ! አንተ የምትኖረው ዐመፀኞች በሆኑ ሕዝብ መካከል ነው፤ እነርሱ ዐመፀኞች ከመሆናቸው የተነሣ ዐይን እያላቸው አያዩም፤ ጆሮም እያላቸው አይሰሙም።
“አንድ ነቢይ ተጠይቆ ሐሰተኛ መልስ ለመስጠት ቢነሣሣ እኔ እግዚአብሔር ያን እንዲያደርግ እተወዋለሁ። ይህንንም ካደረገ ከእግዚአብሔር ሕዝብ መካከል አጠፋዋለሁ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የሕዝቤን አለመታመን ፈውሼ፤ ወደ እኔ እመልሳቸዋለሁ ቊጣዬ ከእነርሱ ስለ ተመለሰ፥ እኔ በገዛ ፈቃዴ እወዳቸዋለሁ፤
ይህም የሚሆነው፥ ‘እነርሱ ወደ እግዚአብሔር ተመልሰው ኃጢአታቸው ይቅር እንዳይባልላቸው፥ ማየትን እያዩ ልብ አያደርጉም፤ መስማትን እየሰሙ አያስተውሉም፤’ ” በተባለው መሠረት ነው።
“የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ መልካም ዜናን ለድኾች እንዳበሥር ሾሞኛል፤ ለታሰሩት መፈታትን፥ ለዕውሮች ማየትን እንዳውጅና የተጨቈኑትንም ነጻ እንዳወጣ ልኮኛል፤
ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “ለእናንተ የእግዚአብሔርን መንግሥት ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኋል፤ ሌሎች ግን ሁሉ ነገር በምሳሌ ይነገራቸዋል፤ እነርሱ እያዩ ልብ እንዳያደርጉ፥ እየሰሙም እንዳያስተውሉ ነው።”
ስለዚህ እነርሱ በቤተ ክርስቲያን ተልከው ሄዱ፤ በፊንቄና በሰማርያ ሲያልፉም የአሕዛብን ወደ እግዚአብሔር መመለስ ተናገሩ፤ ይህም ዜና ክርስቲያኖችን ሁሉ አስደሰተ።
የተናገረውም ቃል ይህ ነው፦ ‘ወደዚህ ሕዝብ ሂድና መስማትስ ትሰማላችሁ፤ ግን አታስተውሉም፤ ማየትስ ታያላችሁ፤ ግን ልብ አታደርጉም በላቸው፤
እግዚአብሔር ግን እስከ ዛሬይቱ ዕለት ድረስ ያለፋችሁበትን ሁኔታ የምታዩበት ዐይን፥ የምትሰሙበት ጆሮ፥ የምታስተውሉበት አእምሮ አልሰጣችሁም።
እነዚህም ሁሉ ከእስራኤላውያን ጋር ጦርነት እንዲገጥሙ እግዚአብሔር ልባቸውን እልኸኛ አድርጎ አነሣሣቸው። ስለዚህም በአጠቃላይ እንዲደመሰሱ ተፈርዶባቸው ያለ ምሕረት ተገደሉ፤ እግዚአብሔርም አስቀድሞ ለሙሴ የሰጠው ትእዛዝ ይኸው ነበር።