ኤርምያስ 46:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጠላት ሠራዊት ኀይል ሲቃረብ ግብጽ እንደ እባብ የፉጨት ድምፅ እያሰማች ትሸሻለች፤ ሰዎች ጥቅጥቅ ያለውን ደን እንደሚመነጥሩ በመጥረቢያ አደጋ ይጥሉባታል። የሰዎቻቸው ብዛት በቊጥር አይደረስበትም፤ የወታደሮቻቸውም ብዛት ከአንበጣ ሠራዊት ይበልጣል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጠላት ገፍቶ ሲመጣባት፣ ግብጽ እንደሚሸሽ እባብ ታፏጫለች፤ ዛፍ እንደሚቈርጡ ሰዎች፣ መጥረቢያ ይዘው ይመጡባታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ጠላቶችዋ በኃይል ዘምተው እንደ እንጨት ቈራጮች በምሳር ይመጡባታልና በደረቱ እንደሚሽሎኮሎክ እባብ ድምፅ ታሰማለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሠራዊትም በኀይል ይዘምቱባታልና፥ እንደ እንጨት ቈራጮችም በምሳር ይመጡባታልና ድምፅዋ እንደምትሸሽ እባብ ይተማል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሠራዊትም ጋር ይሄዳሉና ድምፅ እንደ እባብ ይተምማል፥ እንደ እንጨት ቈራጮችም በምሳር ይመጡባታል። |
መጥረቢያ እንጨት በሚቈርጥበት በባለቤቱ ላይ መነሣት ይችላልን? መጋዝስ በሚሰነጥቅበት ሰው ላይ መነሣት ይችላልን? እንዲሁም በትር በሚይዘው ሰው ላይ ኀይል አይኖረውም።
የሊባኖስ ዛፎችና ዝግባዎች እንኳ ስለ ወደቀው ንጉሥ ደስታቸውን ይገልጣሉ፤ እርሱ ስለ ተወገደ ከእንግዲህ ወዲህ በእነርሱ ላይ መጥረቢያ የሚያነሣባቸው ሰው አይኖርም።
ካለችበት ከጥልቁ ጒድጓድ ትናገራለች፤ ከታች ከትቢያ ውስጥ ንግግርዋ ይመጣል፤ ድምፅዋም እንደ ምትሐት ከምድረ በዳ ይወጣል፤ ከአዋራ ውስጥም ዝቅ ያለ ድምፅዋ ይሰማል።
አገልጋዮችህን ልከህ በጌታ ላይ የስድብ ቃል በመናገር፦ ‘በሠረገሎቼ ብርታት ከፍተኛ የሆኑ የሊባኖስ ተራራዎችን ይዤአለሁ፤ ረጃጅም የሆኑትን የሊባኖስ ዛፎችና የተዋቡ የዝግባ ዛፎችን ቈርጬአለሁ፤ በከፍተኛ ስፍራዎች ላይ ጥቅጥቅ ወዳሉት ደኖች አልፌአለሁ፤
ቅጥረኞች ወታደሮችዋም እንደ ሰቡ ወይፈኖች ናቸው፤ ወደ ኋላ ተመልሰው ይሸሻሉ፤ የፍርድና የጥፋት ቀን ስለ ደረሰባቸው፥ ጸንተው መዋጋት አይችሉም።
ከዚህ በኋላ ሚክያስ እንዲህ አለ፦ “በዚህ ምክንያት ‘ዋይ! ዋይ!’ እያልኩ አለቅሳለሁ፤ ሐዘኔንም ለመግለጥ ራቊቴንና ባዶ እግሬን እሄዳለሁ፤ እንደ ቀበሮ እጮኻለሁ፤ እንደ ሰጎንም የዋይታ ድምፅ አሰማለሁ።
የሊባኖስ ዛፎች ስለ ወደቁ፥ እናንተ የዝግባ ዛፎች “ዋይ!” እያላችሁ አልቅሱ፤ ግርማ የነበራቸው ዛፎች ሁሉ ጠፍተዋል፤ ጥቅጥቅ ያለው ደን ስለ ተቈረጠ የባሳን ወርካዎች “ዋይ!” እያላችሁ አልቅሱ።